ድርጅታችን ፌናኦል ኮፊ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአሁኑ ሰዓት እየተገለገለበት ያለውን ጃፖን ስሪት የሆነ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች ለሚያሟላ ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ፌናኦል ኮፊ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
የተሽከርካሪ ሽያጭ ጨረታ
ድርጅታችን ፌናኦል ኮፊ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአሁኑ ሰዓት እየተገለገለበት ያለውን ጃፖን ስሪት የሆነ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች ለሚያሟላ ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
የተሽከርካሪ አይነት |
የመጫን አቅም |
የተሰራበት ዘመን |
ሞዴል |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
|
ኒሳን ካሽካይ አውቶሞቢል (ጃፓን) |
4 ሰው |
2017 እ.አ.አ |
FRRALJWJ11UG AQADC |
SJNFEJ11U20 10697 |
HRA2*481514* |
- ለጨረታ የቀረበው ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ ነው።
- ጨረታውን በድርጅት ስም የሚጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ንግድ ምዝገባ፣ ንግድ ፍቃድና የድርጅቱን ውክልና እና መታወቂያ ይዞ መቅረብ አለበት።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋቸው ብር 1,500,000.00 (አንድ ሚሊዬን አምስት መቶ ሺህ ብር 100/100) 10% ማለትም 150,000.00 (መቶ ሀምሳ ሺህ ብር100/100) በፌናኦል ኮፊ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም የተዘጋጀ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
- በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚቀርበው ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት ሲሆን የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)15% (አሥራ አምስት በመቶ) በተጨማሪነት ይከፍላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ 5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ንብረቱ በድጋሚ ለጨረታ እንዲቀርብ ይደረጋል። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል።
- የጨረታው አሸናፊ በህጉ መሠረት ለመንግስት የሚከፈለውን ተጨማሪ ዕሴት ታክስን ጨምሮ ማንኛውንም የታክስ ክፍያ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን ከፍሎ ስመ ሀብቱን ወደ እራሱ ማዛወር ይችላል።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት በልደታ ቤተክርስትያን መብራት ገባ ብሎ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ የኢትዮፕያ ንግድ ባንክ ባልቻ አባ ነፍሶ ቅርንጫፍ ሚገኝበት ሳጅዳህ ቢዝነስ ሴንተር ህንፃ አምስተኛ (5) ፎቅ ቢሮ ቁጥር F-5-15 እና F-5-16 በቀጠሮ ማየት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ቢሮ በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ቅዕ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ዋጋ ማቅረብ የሚችሉት የድርጅቱ ማህተም ባረፈበት ዋና የዋጋ ማቀረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት በብቻ ነው። ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ ከጨረታው ውጪ ያስደርጋል።
- በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በአሀዝ እና በፈደል የተጠቀሰው ዋጋ ልዩነት ካለው በፊደል የተጠቀሰው ተቀባይነት ይኖረዋል።
- የጨረታ መነሻ ዋጋው 15% ተ.እ.ታ ያላካተተ ወይም ያልጨመረ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተ.እ.ታ ሳይጨምሩ በዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ በመሙላት በማንኛውም ባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ጋር በኤንቨሎፕ በማሽግ ከመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 17 ቀን 2018 ዓ.ም. 4:00 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው በዚሁ እለት በ4፡30 በተመሳሳይ ቦታ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል። ተጫራቾች በእለቱ ሳይገኙ ቢቀሩን ድርጅቱ ጨረታውን የሚከፈተው ሲሆን ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በአካል በመቅረብ መመለከት ይችላሉ።
- ከፍተኛ ዋጋ ላልስጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል። ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች (የጨረታው አሸናፊ) ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ድርጅቱ ሲያፀድቀው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
- በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙትን የባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለመውድ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ (የመተዳደሪያ ደንብ) ፤ ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት።
- ድርጅቱ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ንብረቱን በሥራ ሰዓት መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በስ.ቁ 09-22-83-73-04 /09-83-49-49-49 ላይ በመደወል ቀጠሮ በማስያዘ መጎብኘት ይችላሉ::
