ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ድርጅታችን ግዮን ሆቴል ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
የግዮን ሆቴል አስተዳደር
ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ግዮን ሆቴል ተሸከርካሪዎችን ጨምሮ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ይህ ማታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በሚታሰብ 15 ቀናት ውስጥ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ ከድርጅቱ ፋሲሊቲ መምሪያ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ::
የጨረታው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል::
→ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር
0115513222 Ext. 5429/5163 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
→ የሥራ ሰዓት፡
ከሰኞ እስከ ሀሙስ ጠዋት 2፡00 - 6:00
ከሰዓት 7፡00 - 11:00
አርብ ጠዋት ከ2፡00 - 5:30 ከሰዓት 7፡30 እስከ 11፡00
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የግዮን ሆቴል አስተዳደር
