በየካ ክ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በየካ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የእንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወያ 001/2018
በየካ ክ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የሠራተኞች ደንብ ልብስ
- ሎት 2. የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 3. ልዩ ልዩ የዕዳት እቃዎች ግዥ
- ሎት 4. አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 5. ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 6. የህከምና መገልገያ ሪኤጀንቶች እና መድሀኒቶች ግዥ
- ሎት 7. የተለያዩ የኤሌክትሮኒከስ ጥገና ስራዎች
- ሎት 8. የህትመት ስራዎች
- ሎት 9. ለህንፃ ፣ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ግዥ
- ሎት 10. ለኢ ኤም አር ኔትወርክ ኢንስታሌሽን ዝርጋታ ሥራ ግዥ
በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች በሙሉ የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል።
1. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድና የፌዴራል ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የእቅራቢነት ዝርዝር መኖራቸውን ማረጋገጫ ደብዳቤ፣ የቫት ተመዝጋቢና ታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
2. ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብርብቻ/በመከፈል ከጤና ጣቢያው ፋይናንስ ከፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ለጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/
ሎት 1. የሠራተኞች ደንብ ልብስ ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
ሎት 2. የደንብ ልብስ ስፌት ብር 3,000.00(ሦስት ሺህ ብር)
ሎት 3. ልዩ ልዩ የፅዳት እቃዎች ግዥ ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
ሎት 4. አላቂ የቢሮ እቃዎች ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
ሎት 5. ቋሚ የቢሮ እቃዎች ብር 10,000.00(አሥር ሺህ ብር)
ሎት 6. የህክምና መገልገያ ሪኤጀንቶች እና መድሀኒቶች ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
ሎት 7. የተለያዩ የኤሌከትሮኒከስ ጥገና ስራዎች ብር 3,000.00(ሦስት ሺህ ብር)ሎት 8. የህትመት ስራዎች ብር 3,000.00(ሦስት ሺህ ብር)
ሎት 8. የህትመት ስራዎች ብር 3,000.00(ሦስት ሺህ ብር)
ሎት 9. ለህንፃ፣ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ግዥ 3,000.00(ሦስት ሺ ብር)
ሎት 10. ለኢ ኤም እር ኔትወርክ ኢንስታሌሽን ዝርጋታ ሥራዎች ግዥ 5,000.00(አምስት ሺ ብር)
ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዳችሁ ጋር በፖስታ ውስጥ ተያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
4. ተጫራቾች የምትጫረተበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ እንደተመለከተው መሠረት ከነቫቱ በማሰብ በፖስታ በማሸግ ማህተም ባረፈበት ኦርጂናል እና ኮፒ እሽግ ለያይቶ በማዘጋጀት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ኮፒ የለሌው ኦርጅናል ሰነድ ውድቅ ይሆናል፡፡
5. የጨረታው ውጤት እንደታወቀ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
6. ጨረታው በእየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሲሆን በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በፋይናንስ ከፍል ይከፈታል፡፡
7. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ጤና ጣቢያው ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው::
8. ተጫራቾች በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
9. ተጫራቶች ከጨረታ መከፈቻ ቀን በፊት ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ለሚቀርብባቸው በያይነቱ ናሙና/ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው:: ናሙና ያልቀረበበት እቃ ዋጋ በሰነዱ ላይ ቢሞሉም ተቀባይነት የለውም፡፡
10. ሎት 7 ላይ የምትወዳደሩ ለጥገና የሚያስፈልገው እቃ በተወዳዳሪ የሚሸፈን ይሆናል፤ ሎት 10 ላይየምትወዳደሩ ቢያንስ 3 ጤና ጣቢያ ላይ ኢኤምአር ዝርጋታ የሰራ እና የሰራበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
11. ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ተወዳዳሪዎች የተደራጃችሁበትን ዘርፍ የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል፡፡
12. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻችን፦ በየካ ከ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ስሙ ቤላ ወይም ጣሊያን ኤምባሲ ጎን የሚገኝ ሲሆን ለበለጠ መረጃ፤ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ ስልከ ቁጥር 0913 60 56 32 ፤ 0913 66 67 47 ወይም 0991 14 08 79
በየካ ክ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ
