የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን ያገልገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ልማትና ማህበራዊ አግልግሎት ኮሚሽን
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን ያገልገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- በጨረታው ማንም ኢትዮጵያ ህጋዊ የሆነ የዜግነት መታወቂያ ያለው ሰው/ድርጅት መወዳደር ይችላል።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 2000 (ሁለት ሺህ) ከፍለው የተሽከርካሪዎችን ዶክሜንት አዲስ አበባ ኮሚሽኑ ዋና ጽ/ቤት ግቢ ከ መስከረም 11 /2018 እስከ መስከረም 26/2018 ዓ/ም ድረስ ዘወትር በስራ ቀናትና ሰዓት ቀርቦ መግዛት ይችላሉ
- የጨረታው አይነቶች
- 1ኛ መኪኖች ባሉበት ሁኔታ
- 2ኛ ሞተር ሳይክሎች ባሉበት ሁኔታ
- 3ኛ ለውሃ ቁፋሮ አግልግሎት የሚሰጡ መኪኖች ባሉበት ሁኔታ (150 ሜትር መቆፈር የሚችል) ውሃ መቆፈሪያ ማሽን፤ ለዚሁ አገልግሎት የሚውል ኮምፕሬሰር ባለበት ሁኔታ
- ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት።
- 1ኛ አዲስ አባባ ላፍቶ ክ/ከተማ መካኒሳ ጀርመን አደባባይ አካባቢ መካነ ኢየሱስ (ጉዲና ቱምሳ ሁለገብ ማሰልጠኛ ማእከል) ግቢ
- 2ኛ ኦሮሚያ ክልል ነቀምት መካነ ኢየሱስ ግቢ
- 3ኛ ትግራይ ክልል መቀሌ መካነ ኢየሱስ ግቢ
- 4ኛ ኦሮሚያ ክልል ቡሌ ሆራ ከተማ መካነ ኢየሱስ ግቢ
- 5ኛ ኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ዶዶላ ከተማ መካነ ኢየሱስ ግቢ ናችው።
- ተጫራቾች ዋጋ የሚያቀርቡት በተሽከርካሪዎች ዝርዝር በተዘጋጀው ሠንጠርዥ ላይ ነው።
- ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ጨረታው ከወጣበት ከመስከረም 11 /2018 እስከ መስከረም 26/2018 ዓ/ም ዘወትር በሥራ ቀናት ብቻ በተራ ቁጥር 4። ላይ የተገለጹበት ቦታዎቸ በመሄድ ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የተወዳደሩትን የጨረታ ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አዲስ አበባ አራዳ ክ/ከ አምስት ኪሎ አካባቢ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋካሊት ፊት ለፊት በሚገኘወ የልማአኮ ዋና ጽ/ቤት እስከ መስከረም 15/2018 ዓ/ም ከቀኑ አሥር ሰአት ድረስ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለተሽከርካሪዎቹ የሰጡትን ዋጋ 30% (ሰላሳ በመቶ) ሲፒኦ (CPO) በ EECMY DASSC ስም ባንክ በማስያዝ ከጨረታው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ከተቀመጠለት መነሻ ዋጋ በታች ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ቀጥታ ከውድድሩ ያስሠርዛል።
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪልና ያላቸው ሰዎች በተገኙበት መስከረም 27/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት በልማአኮ ዋና ጽ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በአሥር ቀን ውስጥ በማስታወቂያ ቦርድ ላይ በሚለጠፈው በማስታወቂያና በደብዳቤ የጨረታው አሸናፊ ይገለጻል።
- አሽናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጠበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ በድርጅቱ አካውንት ገቢ በማድረግ ንብረቱን ካልተረከበ ያስያዙትን ሲፒኦም ሆነ ንብረት መጠየቅ/ማግኘት አይችሉም።
- የጨረታው አሸናፊ ማንኛውንም ተያያዥ የመንግስት ወጪዎችን በራሱ ይሸፍናል።
- ድርጅቱ ከዕዳና እገዳ ውጭ ከሽያጩ በኋላ ለሚከሰቱት ማንኛውም ወጭዎች ድርጅቱ ተጠያቂ አይሆንም።
- ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን ዋና ጽ/ቤት
አዲስ አበባ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የቤት ቁጥር 922 አምስት ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ፋካሊቲ ፊት ለፊት
ስልክ 0911306233, 0911552954
