የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የጽህፈት እቃዎች ግዢ በግልጽ ጨረታ መፈጸም ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2018 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ግዥዎችን መፈጸም ይፈልጋል።
- አላቂ የጽህፈት እቃዎች፣
ስለሆነም፡-
- በ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2% በማሰብ በታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ኦርጂናሉን እና ኮፒውን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 4 ፊት ለፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከቀረበው /specification/ ውጭ በመሰረዝ ወይም በማሻሻል ማቅረብ እንዲሁም በሌላ ተጫራች ዋጋ ተንተርሶ መጫረት አይፈቅድም፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በተሰጠው የጨረታ ሰነድ /specification/ መሰረት እቃውን ለማቅረብ ውለታ ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ በማቅረብ በሚመለከታቸው የኮሌጁ ባለሙያዎች እየተረጋገጠ ለኮሌጁ ንብረት ክፍል በሞዴል 19 ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል።
- የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 12 ጨረታው ይከፈታል፣ ሆኖም የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓላ ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል።
- ኮሌጁ የቫት ሰብሳቢ መ/ቤት ስለሆነ 7.5% ቫት ቆርጦ ህጋዊ ደረሰኝ ይሠጣል።
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ስልክ ቁጥር፡- 033-112-44-16
ፋክስ ቁጥር፡- 033-111-84-680
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ጥበቃ ቢሮ የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
