በኢፌዲሪ ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የግዥ አይነት፦ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና የአደጋ መከላከያ ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኮማማኢ/ሰቼማ/001/2018
በኢፌዲሪ ኢትዮ ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የግዥ አይነት፦ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች እና የአደጋ መከላከያ ዕቃዎች የተጫራቾች መመሪያና ግዴታ:-
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN NO/ያላቸው፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /NAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ VAT ጨምረው ብር2% በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ (CPO) ወይም የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት ከዚህ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ይሆናል፣ በዋጋ መሙያ ቅፅ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ እጅግ የተከለከለ ነው፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡
7. የመወዳደሪያ ሰነዱን የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመከፈል በቂርቆስ ከፍለ ከተማ ከላንድ ማርከ ሆስፒታል ትይዩ በሚገኘው ጠማማ ፎቅ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 15 አንደኛ ፎቅ ላይ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በቀረበው ዝርዝር በመሙላት የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ኢንዱስትሪው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡
9. የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
10. የጨረታ መከፈቻ ቀን በሕዝብ በዓላት ቀን ከዋለ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ በዓሉ በዋለ በማግስቱ ይሆናል፡፡
11. ጨረታው ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት በጨረታ ሰነድ ላይ የሚጠቀስ ይሆናል፡፡
12 የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለፀለት በኃላ በሦስት ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል በመዋዋል ንብረቱን በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ ማቅረብ አለበት፡፡
13. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን አርጅናሉንና ኮፒዉን ለየብቻ በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
14. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
15. አድራሻ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ትይዩ በሚገኘው ጠማማ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 አንደኛ ፎቅ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-23-80-19-15/09-40-81-62-06 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩኘ የኮንስትራክሽን
ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
