በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግ እና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዩኒት ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ የተለያዩ የማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ፈልጎ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-EEP/EC/FP/NCB/03/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግ እና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዩኒት ፋይናንስ እና ግዥ መምሪያ የተለያዩ የማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ ለመፈፀም ፈልጎ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው የመ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል 2ኛ ፎቅ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ/ ብር በመክፈል ኢንጂነሪንግ እና ኮንስትራክሽን ቢዝነስ ዘርፍ ግዥ ከፍል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ዕቃዎች የቴክኒከና የፋይናንሽያል ሰነዳቸውን የጨረታ ቁጥር EEP/EC/FP/NCB/03/2018 በግልጽ ከዚህ በታች በተቀመጠው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
|
ተ.ቁ |
የጨረታ ቁጥር |
የግዥው አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታው መክፈቻ ቀን
|
|
1 |
EEP/EC/FP/NCB/03/2018
|
የተለያዩ የማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች |
50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ |
መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት |
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ግቢ ውስጥ ኢንጅነሪንግ እና ኮንስትራክሽነ ቢዝነስ ዘርፍ ግዥ ቢሮ በአካል በመገኘት መጠየቅ እና በተጨማሪ በስልክ ቁጥር +251 11 6732198 መደወል ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
