የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ልማትና በጎ አድራጎት ድርጅት የተባለ አገር በቀል ድርጅት ድርጅቱ በአዋጅ ቁጥር 113/201 አንቀጽ 88/3 መሰረት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዳግም ተመዝግቦ በመዝገብ ቁጥር 1417 ህጋዊ ሰውነት ያለው ሀገር በቀል ምግባረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅታችን አንድ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ልማትና በጎ አድራጎት ድርጅት
በድጋሚ የወጣ የሊፋን መከና ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ልማትና በጎ አድራጎት ድርጅት የተባለ አገር በቀል ድርጅት ድርጅቱ በአዋጅ ቁጥር 113/201 አንቀጽ 88/3 መሰረት በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዳግም ተመዝግቦ በመዝገብ ቁጥር 1417 ህጋዊ ሰውነት ያለው ሀገር በቀል ምግባረ ሰናይ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅታችን አንድ ተሽከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች፡-
1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በወጣ ከ2ኛው ቀን በኋላ ንብረቶቹ በሚገኙበት ከኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ልማትና በጎ አድራጎት ድርጅት በመገኘት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20% የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
3. የጨረታ አሸናፊዎች ጨረታው በጸደቀ በ3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ሲያስገቡ ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ይመለስላቸዋል፡፡
4. የጨረታ ተሸናፊዎች ጨረታው በጸደቀ በ3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ይመለስላቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሠነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በአድራሻችን ማስገባት አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት /15/ ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡ በአስራ አምስተኛው /15/ቀን የጨረታ ሰነዱ የሚገባው እስከ 5፡00
የኢትዮጵያ ገነት ቤተክርስቲያን ልማት ና በጎ አድራጎት ድርጀት
