Tender Detail

Tender Details


የሰበታ ክፍለ ከተማ የሞግሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለወራዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ለወራዳ ማዘጋጀ ቤት እገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ ጽዳት እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፤ ደንብ ልብሶች፤ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መወዳደርየምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡

የሰበታ ክፍለ ከተማ የሞግሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አንድ (1)

የሰበታ ክፍለ ከተማ የሞግሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለወራዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ለወራዳ ማዘጋጀ ቤት እገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፤ ጽዳት እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች፤ ደንብ ልብሶች፤ ኤሌክትሮኒክስ እና ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መወዳደርየምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባችውን የዘመኑን ግብርአጠናቀው ስለመከፈላቸው በቂ ማስረጃ (ከሊራንስ) ከሚመለከተዉ እካል ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይየስራ ቀናት በሲንቄ ባንክ ሂሳቢ ቁጥር በ “Mogle Wereda Finance Office" "1065278471215" የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) በሎት አንድ(1)ና ሁለት ለየብቻ ገቢ በማድረግ የሞግሌ ወረዳ ገቢዎች ወይም የሞግሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመሄድ ወደ ደረሰኝ በማስቀየር ዘወትር በስራ ሰዓት የሞግሌ ወረዳ ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት መግዛት ይችላል፡፡

3. ተጫራቾች የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በተዘጋጀው ሰነድ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ከጀርባ የባንክ ስልክ ቁጥር፤ አርማና ቅርንጫፍ የሞግሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር እያይዘው ማቅረብና ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ባሸነፈበት መጠን የውል ማስከበሪያ 10% በሎት አንድ(1)ና ሁለት ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

5. ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ የሚሸጡበትን ዋጋ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት፡፡

7. ለጨረታ በሚያቀርቡት በእያንዳንዱ የሰነዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ስምና አድራሻ የሚገልጽ ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ ማስፈር አለበት፡፡

8. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃዎች ገቢ የሚሆነው አስፈላጊውን ጥራት ማሟላቱን በባለሙያ እና ጥራት አጣሪ ኮሚቴ ሲረጋገጥ ብቻ ይሆናል፡፡

10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ በመጋዘን ቀድመው ማከማቸት ይኖርባቸዋል፡፡

11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት ናሙናውን ማቅረብ አለባቸው፡፡

 

12. የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

13. ከላይ የተገለጸው የመከፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል፡፡

14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0913841577/0913911437/

የሰበታ ክ/ከተማ የሞግሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender