Tender Detail

Tender Details

  • Company Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
  • Address አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0114420688
  • Websitehttp://www.mughercement.com.et/
  • Deadline30 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price575.00
  • Bid Security600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ ብር)
  • opening date2025-09-30 00:00:00
  • Categories Transportation Service And Cargo

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ትራንስፖርት (ፑሚስ፣ ክሊንከር፣ ጅፕሰም) እና ሲሚንቶ የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡

Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)


 

የሀገር ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር ሙሲፋ /58/2017

 

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ትራንስፖርት (ፑሚስ፣ ክሊንከር፣ ጅፕሰም) እና ሲሚንቶ የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የንግድ ምዝገባና ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2017/18 ዓ/ም) የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ሰነዶች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖረሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በገዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡

ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ 0114420216

ፋክስ 0114420688

 

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ

 

Save Tender