በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ አገልግሎት የሚውል አንድ ጀነሬተር ግዥ ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 03/2018
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ አገልግሎት የሚውል አንድ ጀነሬተር ግዥ ከዚህ በታች በቀረበው መሰረት ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈርት መሰረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታክስ ክሊራንስ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና የታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዲሁም የተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ርዳይሬከቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00- 6፡00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ9ዐ ቀን ጸንቶ የሚቆይ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በሲፒኦ ወይም አንኮንድሽናል የባንክ ዋስትና በማቅረብ መወዳደር አለባቸው፤
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጊዜ በሁለት ኮፒ እና አንድ ኦርጅናል ፖስታ በማሽግ ቴከኒካል፣ ፋይናንሻል የጨረታ ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኦርጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ውስጥ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት/ ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ከግዥ ክፍል 14 ቁጥር ማግኘት ይቻላል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሀያ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነው ግዥ 50% ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 046-221-70-02/03
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ
ሀዋሳ
