ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ያገለገሉ የተለያዩ አይነት ፎርክሊፍቶችን፣ ኢምፒቲ ኮንቴይነር ማንሻ ማሽኖችን፣ የተርሚናል ትራክተሮችን፣ የውሃ ታንከርትሬለርን፣ ትራከተርን፣ ሪችስታከርን፣ትራከተርን፣ ታይር ሪካፕ ማሽነሪን፣ ኮንከሬን ማሽንንና የማሽነሪ መለዋወጫ የሆኑ የማሽን ሞተር፣ ጊርቦከስ፣ ሃይድሮሊክ ሲሊንደር ፒስተን፣ ለፍቲነገ ሲሊንደር፣ ስቲሪንግ ሲሊንደር፣ ትራንስሚሽን ጊር ቦክስ እንዲሁም የማሸነሪ አታችመንት የሆኑ ፔፐር ሮል ከላምፕን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ቅዳሜ ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት ጨረታው አርብ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያቤት እንደሚከፈት የተመላከተ ቢሆንም ከህዝባዊ በአላት ጋር ተያይዞ ለተጫራቾች በቂ ጊዜ ለመስጠት እንዲቻል የጨረታ መከፈቻ ቀኑን ማራዘም አስፈልጓል፡፡
Ethiopian Shipping and Logistics (የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ)
የኢትየጲያ የባህር ትራንስፖርት ሎጅስቲክስ
ግልፅ የጨረታ ሽያጭ ማራዘሚያ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ - DIS 01/2017
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ያገለገሉ የተለያዩ አይነት ፎርክሊፍቶችን፣ ኢምፒቲ ኮንቴይነር ማንሻ ማሽኖችን፣ የተርሚናል ትራክተሮችን፣ የውሃ ታንከርትሬለርን፣ ትራከተርን፣ ሪችስታከርን፣ትራከተርን፣ ታይር ሪካፕ ማሽነሪን፣ ኮንከሬን ማሽንንና የማሽነሪ መለዋወጫ የሆኑ የማሽን ሞተር፣ ጊርቦከስ፣ ሃይድሮሊክ ሲሊንደር ፒስተን፣ ለፍቲነገ ሲሊንደር፣ ስቲሪንግ ሲሊንደር፣ ትራንስሚሽን ጊር ቦክስ እንዲሁም የማሸነሪ አታችመንት የሆኑ ፔፐር ሮል ከላምፕን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ቅዳሜ ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት ጨረታው አርብ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያቤት እንደሚከፈት የተመላከተ ቢሆንም ከህዝባዊ በአላት ጋር ተያይዞ ለተጫራቾች በቂ ጊዜ ለመስጠት እንዲቻል የጨረታ መከፈቻ ቀኑን ማራዘም አስፈልጓል፡፡
በመሆኑም በዚህ የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማራዘሚያ ማስታወቂያ መሰረት የማራዘሚያ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ሐሙስ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሠዓት ከ8፡00 እስከ 11፡ 00 ሰዓት እና ሐሙስ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከ2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ለገሀር ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ በመከፈል ሰነዱን ከ6ኛ ፎቅ መውሰድና በጨረታ ሂደቱ መሳተፍ ይቻላል፡፡
የግልፅ ጨረታው ሐሙስ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 6ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል፡፡
በጨረታ መከፈቻው ሰዓት፣ እለትና ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር on-5-54-93-04 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ
