በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ትራንስፖርት (ፑሚስ፣ ክሲንከር፣ ጅፕሰም) እና ሲሚንቶ የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡
Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory (በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ)
የሀገር ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ሙሲሩ /58/2017
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት የሚውል የጥሬ ዕቃ ትራንስፖርት (ፑሚስ፣ ክሲንከር፣ ጅፕሰም) እና ሲሚንቶ የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የንግድ ምዝገባና ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው (የ2017/18 ዓ/ም) የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እና የታክስ ከፋይ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጠቀሱትን ሰነዶች ኮፒ በመያዝ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 575.00 ከነቫቱ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ በቅሎ ቤት አካባቢ ጋራድ ህንፃ ቢሮ ቁጥር 432-3-8 ከሚገኘው የግዥ መምሪያ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 600,000.00 (ስድስት መቶ ሺህ ብር) በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖረሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ (Chemical Industry Corporation Mugher Cement Factory) ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (C.P.O) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒክ ዶክመንቶቹ ጋር በማያያዝ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጀምሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸውን አዲስ አበባ በሚገኘው በግዥ መምሪያ ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በግዥ መምሪያ ቢሮ ይከፈታል፡፡
ፋብሪካሙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በኪሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
ስልክ 0114420216 /ፋክስ 0114420688
አዲስ አበባ
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ
