የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን የ2018 በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎት የተለያዩ መጠን ያላቸው ማሽነሪ እና ቀላልና ከባድ ተሸከሪካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር፡- ሲ/መ/ባ/001/2018
የሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን የ2018 በጀት ዓመት ለሥራ አገልግሎት የተለያዩ መጠን ያላቸው ማሽነሪ እና ቀላልና ከባድ ተሸከሪካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
Unity |
QTY |
Remark |
|
1 |
Battery 12v90AH |
pc |
04 |
140k grader, Cat Dozer |
|
2 |
Battery 12v150AH |
pc |
06 |
Dump truck 950H Loader |
|
3 |
Battery 12v100AH |
Pc |
04 |
XCMG ROLLER & Excavator |
|
4 |
Battery 12v110AH |
Pc |
04 |
Volvo grader |
|
5 |
5 Battery 12v70AH |
Pc |
08 |
Light vehicles |
|
6 |
Battery 12v250AH |
Pc |
04 |
Liheber machinery |
|
7 |
Battery 12v250AH |
pc |
04 |
Hyundia dump truck |
ስለዚህ፡-
- በተጠየቀው መሰረት የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገፅ መመዝገብ ወይም በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር-5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (uncondition-al Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 0.5% ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሠረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፋይናንሻል አንድ ዋና ወይም ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና /ኦርጅናል/ እና ሁለት ኮፒ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁሉም ዶክሜንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰአት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአየር ላይ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተጠቀሰው የመክፈቻ ቀን የእረፍት ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከወድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረሳል ወደፊትም መ/ቤቱ በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታው የሞሉትን የመወዳደሪያ ዋጋ ከተከፈተ ቀን ጀምሮ የጨረታው ሂደት ተጠናቅቆ ከአሸናፊው ጋር ውል እስከሚፈጸም ድረስ ጸንቶ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ለባለሥልጣን መ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታከስ የሚያካትት መሆኑን እና አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል ፡፡
- በጨረታው ሰነድ ላይ የተጠቀሱትን የጨረታ መመሪያ እና ሕጎች አለማከበር በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ስርዝ ድልዝ ያለበት ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446
ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን
