በአ/ብ/ክ/መ የኦሮ/ብ/ዞን/የባቲ/መ/ደ/ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎች፣ የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣ የተለያዩ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ እስቴሽነሪ፣ የጥበቃና የጽዳት ሰራተኞች (አውትሶርስ) በማህበር የተደራጁ፣ የኤሌትሪክ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
በአብክመ የኦሮ/ብ/ዞን የባቲ መ/ደ/ሆስፒታል
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም
በአ/ብ/ክ/መ የኦሮ/ብ/ዞን/የባቲ /መ/ደ/ሆስፒታል በ2018 በጀት አመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል
- የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎች
- የተለያዩ ፈርኒቸሮች
- የተለያዩ የጽዳት እቃዎች
- ኤሌክትሮኒክስ
- እስቴሽነሪ
- የጥበቃና የጽዳት ሰራተኞች (አውትሶርስ) በማህበር የተደራጁ
- የኤሌትሪክ እቃዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በቀረበው ዝርዝር መሰረት፡-
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘረፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስረከቢያ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ በአደራ መቀበያ ደረሰኝ በባቲ/መ/ደ/ሆስፒታል በምርጫቸው በአንዱ ከዋናው ኦርጅናል የማወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- CPO የጨረታ ማስከበሪያ ከተራ ቁጥር 1-2 ለተገለጹት የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 20,000/ ሃያ ሺብር /ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የገንዘብ መጠኑ ከ200,000 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ2/1/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት እስከ 15 ኛው ቀን ማለትም 17/1/18 ዓ.ም ከ11፡30 ሰአት ድረስ በባቲ/መ/ደ/ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 54 ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የማወዳደሪያ ሀሳባቸውን ዋናው ቅጅ ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ2/1/2018 ዓ.ም ጀምሮ አስከ 16ተኛው ቀን ማለትም እስከ 19/1/18 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ብቻ በባቲ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 በግልጽ ይከፈታል።
- ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት ጨረታውን በጥቅል ዋጋ /ሎት/ የሚያወዳድር መሆኑንና ሙሉ ጨረታ ሰነድ ዋጋ ያልሞላ ከጨረታ ውድድር ውጭ የሚሆን መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች በሰነዱ ላይ ስም ማህተምና ፊርማ አሟልተው መገኘት አለባቸው። ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊ ድርጅቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ ደብዳቤ መ/ቤቱ የምናሳውቅ ይሆናል
- ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብ የተጠበቀ ነው
ስለጨረታው የበለጠ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ በባቲ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 09 20 79 72 71 ወይም 09 10 17 73 45 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ የኦሮ/ብ/ዞን የባቲ መ/ደ/ሆስፒታል
