Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address ጅግጅጋ ከተማ ፡ ሶማሌ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0913220473
  • Website
  • Deadline22 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር)
  • opening date2025-09-22 00:00:00
  • Categories Vehicle

የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት መስጠት የሚችል አንድ ካስተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር ECCJBO 02/2018

 

የጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የሰራተኞች ሰርቪስ አገልግሎት መስጠት የሚችል አንድ ካስተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡-
  2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡-
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡-
  4. ተሸከርካሪው ሙሉ አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ካስተር ለ30 ሰውና ከዚያም በላይ የመጫን አቅም ያለው።
  5. የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ያለውና ግብር የነበረ የመንገድ ትራንስፖርት ቦሎ ያለው
  6. ተጫራቾች ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ፣ እሁድ ሙሉ ቀን እና በካላንደር ዝግ በሆኑ ቀናቶች ክፍያና ስራ የሌለ መሆኑን አውቆ የሚጫረት ሆኖ መ/ቤቱ ለስራ ከፈለገው የሚሰራ
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በንግድ ባንክ የተመሰከረለት (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችሉ፡
  8. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለጨረታ ሰነዱ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነዱን ከጅግጅጋ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ከገቢ ሒሳቦች ቡድን መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ አንቨሎፕ ቴክኒካል እና ፋይናሻል ለየብቻ ከአንድ ኮፒ ጋር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በጨረታው ቀን ብቻ እስከ ጠዋት 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላል
  10. ጨረታው ማስታውቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት 1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 05 ጨረታው ይከፈታል፡፡ 11ኛ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን ጨረታው ይካሄዳል፡፡
  11. ተጫራቾች በጨረታው ቀን የሚወዳደሩበት ተሽከርካሪ በአካል ወይም በቪዲዮ መቅረብ ይኖርበታል።
  12. አሸናፊው ድርጀት የማሽከርከር ፍቃድ ያለው ሾፌር ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻችን ፡- በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ግዢና ፋይናንስ ቡድን

1ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 05 መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0913841834 ወይም 0910208950

E-mail address jijccarchive@gmail.com ወይም Getachewtakt@gmail.com

 

ጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender