በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች ለአገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያ በመስኩ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች ለአገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያ በመስኩ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
- በመስኩ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
- ቲን ነምበር ያላቸው
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ
- በመንግስት ግዢ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ
- የጨረታ ዋስትና 50,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ከወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 0467710211 ይደውሉ፡፡
በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
