Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)
  • Address ቦሌ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115174918
  • Websitehttps://corporate.ethiopianairlines.com/
  • Deadline02 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security100,000
  • opening date2025-10-02 00:00:00
  • Categories Furniture

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለወንጪ ኢጃ ኢኮ ሎጅ ጣቢያ የተለያዩ የፈርኒቸር እና ተያያዥ ምርቶችን (purchase of different furniture and other related products to Wonchi lja Eco Lodge tent projects) የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መስራት ይፈልጋል፡፡

Ethiopian Airlines Group (የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ)


                                                  የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር: GGP -T575 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለወንጪ ኢጃ ኢኮ ሎጅ ጣቢያ የተለያዩ የፈርኒቸር እና ተያያዥ ምርቶችን (purchase of different furniture and other related products to Wonchi lja Eco Lodge tent projects) የሚያቀርቡ  ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መስራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፦

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት/TIN/ ያላቸው እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ 

  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው } ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ ቅርንጫፍ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር GGP - T575 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ቅጅ (Deposit Slip Copy) ፣ የጨረታውን ቁጥርና አይነት እንዲሁም የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ ከታች በተጠቀሰው የኢሜል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በኢሜል ማግኘት ይችላሉ፡፡ 

  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ ተቋም እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል፡፡ 

  4.  ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ150 ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡ አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው፡፡ 

  5. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጨረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ በተለያየ ኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ግዥ ከፍል እስከ መስከረም 22/2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ በ9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ግዥ ክፍል ግሩፕ ጀነራል ፐርቼዝ ስልክ ቁጥር፡ +251-115-17-46-55 A-EmiruG@ethiopianairlines.com አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

Save Tender