የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሚያመርተው ቬኒር እና ፕላይ ውድ ጣውላ ግብዓት የሚሆን የባህርዛፍ ግንድ ጫካው ከሚገኝበት ከደ/ብርሃን ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ ከሚገኘው ባቄሎ ቀበሌ ጎደፊት አካባቢ ደን ሳይት የተቆረጠ ግንድ የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን በዘርፉ የተሰማሩ ባለንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ባለንብረት ጋር የኮንትራት ውል በመግባት ግንዱ ተጭኖ እስከሚያልቅ ድረስ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡
Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለሚያመርተው ቬኒር እና ፕላይ ውድ ጣውላ ግብዓት የሚሆን የባህርዛፍ ግንድ ጫካው ከሚገኝበት ከደ/ብርሃን ወደ ደሴ በሚወስደው መንገድ ከሚገኘው ባቄሎ ቀበሌ ጎደፊት አካባቢ ደን ሳይት የተቆረጠ ግንድ የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖችን በዘርፉ የተሰማሩ ባለንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ከሆነው ባለንብረት ጋር የኮንትራት ውል በመግባት ግንዱ ተጭኖ እስከሚያልቅ ድረስ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፡-
- በዘርፉ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሰ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያላቸው
- የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሁለቱም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 40,000.00 /አርባ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፈርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
- ድርጅቱ ክፍያ የሚፈፅመው በቢያጆ ስለሆነ ለመኪናው የሚያስፈልገውን ወጭ የነዳጅ እና ሌሎች ሁሉንም ወጭዎች የሚሸፍነው ባለመኪናው ይሆናል፣
- ተጫራቾች አሪጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ውስጥ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ስለሆነ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም፡፡
- የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ወይም እሁድ ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 0910368437 ደውለው ይጠይቁ
የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር
ደብረ ብርሃን
