የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ በአሰላ፣ በሀዋሳ እና በባህርዳር ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል ለመሸጥ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- ኢግስኮ-ምዘአዘ/ጨሽ/04 ሰነድ/2017
የኢትዮጵያ ምርጥ ዘርና የደን ውጤቶች አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ በአሰላ፣ በሀዋሳ እና በባህርዳር ቅ/ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ፡
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላችሁ እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፤
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ ስም የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ በCPO ብቻ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሱት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም ከአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የተገለፀውን መጠን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጫረት ይችላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የምግብ እህሉ እና የብጣሪ እህሉ በሚገኙበት ቅ/ጽ/ቤቶች በመገኘት አይቶ መጫረት አለበት። ይህን ሳያደርግ ዋጋ ቢያቀርብ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
- የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጠን በዚህ ጨረታ ሠነድ ላይ ከተገለፀው መጠን ሊያንስ ይችላል።
- ዋጋውን በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው መስከረም 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ ጽ/ቤት አዳራሽ እና ከላይ በተጠቀሱት ቅ/ጽ/ቤቶች ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
ስልክ ቁጥር፡- 011-6-18-61-25 አዲስ አበባ
በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
