Tender Detail

Tender Details

  • Company የወንዶ ትራንስፖርት ኩባንያ
  • Address ሲዳማ ዞን ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462209024
  • Website
  • Deadline13 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-09-13 00:00:00
  • Categories Vehicle

የወንዶ ትራንፖስርት ኩባንያ በ2018 በጀት ዓመት ከተለያዩ ፋብሪካዎች/ማዕከሎች ሲሚንቶ፤አልሚ ምግብ እና ለሎች ጭነቶችን በግልጽ ጨረታ ህጋዊ የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

የወንዶ ትራንስፖርት ኩባንያ


                               ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

                                    የጨረታ ቁጥር ወትኩ/001/2018

 የወንዶ ትራንፖስርት ኩባንያ በ2018 በጀት ዓመት ከተለያዩ ፋብሪካዎች/ማዕከሎች ሲሚንቶ፤አልሚ ምግብ እና ለሎች ጭነቶችን በግልጽ ጨረታ ህጋዊ የደረቅ ጭነት የትራንስፖርት ድርጅቶችን አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡- 

  1. በደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማረጋገጫ የሚያቀርቡ ተጫራቾች። 

  2.  በጨረታው ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታው ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ሀዋሳ መናኸሪያ ክ/ከተማ ዳእቴ ካፌና ሬስቶራንት ፍትለፍት በሚገኘው ወንዶ ኩባንያ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ከግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር መምሪያ በመቅረብ ወይም አዲስ አበባ ከሚገኘው ቢሮአችን ፊንፊኔ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። 

  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመስሪያ ቤቱ ፍላጎት መሰረት ብቻ በመሙላት የተሟላ የመወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በሁለት የተለያየ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 

  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት አየር ላይ ውሎ በ8ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በ8፡10 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/መምሪያ ቢሮ በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም 8ኛዉ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል። 

  5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታ መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ከጨረታ ራሱን ማግለል አይችልም። 

  6. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። 

  7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462209024 ወይም 0916860565/0912780926 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

           የመ/ቤቱ አድራሻ - ሀዋሳ መናኸሪያ ክ/ከተማ ዳእቴ ካፌና ሬስቶራንት ፍትለፍት በሚገኘው ወንዶ ኩባንያ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ። 

                                                                         የወንዶ ትራንስፖርት ኩባንያ

Save Tender