የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/FPGS/NCB/01/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን የአቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝርድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት፣ የውጭ ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥ ቢሮ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ዕቃዎች በሚመለከት የመወዳደሪያ ስነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/FPGS/NCB/01/2018 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው የአቅርቦት ግዥ መወዳደር ይችላሉ፡፡
|
የአቅርቦት ግዥ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ስዓት |
የጨረታው መከፈቻ ቀንና ስዓት |
|
Three Axle Cargo Semi Trailer (ሃይቤድ ተሳቢ) |
ብር 140,000.00
|
መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡ oo ስዓት |
መስከረም 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡01 ስዓት |
ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-5 58 17 25 /011-5 5819 16 መደወል ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
