በሲዳማ ክልል የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018ዓ.ም በጀት ዓመት ለሴከተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የእስቴሽነሪ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሲዳማ ክልል የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
የጨረታማስታወቂያ
በሲዳማ ክልል የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018ዓ.ም በጀት ዓመት ለሴከተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የእስቴሽነሪ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት ተጫራቾች ማሟለት የሚያስፈልጋቸዉ ተግባራት፡-
1. በዘርፉ የንግድ ፍቃድ ያላቸው በ2018ዓ.ም ፍቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
2. ተጨማሪ እሰት ታክስ 15% VATተመዝጋቢ የሆነ
3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
4. በዕቃው አቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
5 የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ ግዥ 10,000/ አሥር ሺህ ብር ብቻ! የኢትዮጵያ ብር በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ CPO በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
6 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ብቻ ለገቢዎች ባለሥልጣን ቅ/ጽ/ቤት በመቅረብ ከፍሎ የተከፈለበትን ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነድ ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
7. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልተው በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በሁሉም ዶክመንት ላይ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. የጨረታው ሰነድ የሚከፈትበት በ16ኛው ቀን በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።
9. የጨረታው አሽናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
10. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያቀረበውን ዕቃ ጥራቱን ያልጠበቀ ከሆነ ዕቃ የተገዛበትን ገንዘብ የመመለስና ወይንም ዕቃ የመለወጥ ግዴታ አለበት፡
11. አሰሪ መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ የሚቀጥለው በሥራ ቀን ይከፈታል።
13. የወቅቱን ዋጋ ያላገናዘበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
በሲዳማ ክልል የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት
