ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ያገለገሉ የተለያዩ አይነት ፎርከ ሊፍቶችን፣ ኢምፒቲ ኮንቴይነር ማንሻማሸኖችን፣ የተርሚናል ትራክተሮችን፣የውሃ ታንከርትሬለርን፣ትራከተርን፣ ሪች ስታከርን፣ ትራከተርን፣ ታይር ሪካፕ ማሽነሪን ኮንከሬን ማሽንንና የማሽነሪ መለዋወጫ የሆነ የማሽን ሞተር ጊርቦክስ፣ ሃይድሮሊክ ሲሊንደር ፒስተን፤ ሊፍቲንግ ሲሊንደር፣ ስትሪንግ ሲለንደርትራንስሚሽን ጊር ቦክስ እንዲሁም የማሽነሪ አታችመንት የሆነ ፔፐር ሮል ከላምፕን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Ethiopian Shipping and Logistics (የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ)
ያገለገለ ማሽነሪዎችና መለዋወጫዎች የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ
የጨረታ ቁጥር DIS 01/2017
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ያገለገሉ የተለያዩ አይነት ፎርከ ሊፍቶችን፣ ኢምፒቲ ኮንቴይነር ማንሻማሸኖችን፣ የተርሚናል ትራክተሮችን፣የውሃ ታንከርትሬለርን፣ትራከተርን፣ ሪች ስታከርን፣ ትራከተርን፣ ታይር ሪካፕ ማሽነሪን ኮንከሬን ማሽንንና የማሽነሪ መለዋወጫ የሆነ የማሽን ሞተር ጊርቦክስ፣ ሃይድሮሊክ ሲሊንደር ፒስተን፤ ሊፍቲንግ ሲሊንደር፣ ስትሪንግ ሲለንደርትራንስሚሽን ጊር ቦክስ እንዲሁም የማሽነሪ አታችመንት የሆነ ፔፐር ሮል ከላምፕን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በግልፅ ጨረታው በመሳተፍ ለመወዳደርፍቃደኛ የሆነ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ቅዳሜ ጳጉሜ 1 ቀን 2017ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት አርብ መስከረም ቀን 2018ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 እና ከሠዓት ከ 8፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እና አርብ መስከረም 9 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ የማይመለስ ብር1000.00 (አንድ ሺህ) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ለገሀር ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያቤት 3ኛ ፎቅ በመከፈል ሰነዱን ከ6ኛ ፎቅ መውሰድና በጨረታ ሂደቱ መሳተፍ ይቻላል።
ተጫራቾች ንብረቶቹን ለማየት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቅዳሜ ጳጉሜ ፡ ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት አርብ መስከረም 9 ቀን 2018ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 እና ከሠዓት ከ 8፡00 እስከ 11፡ዐዐ ሰዓት እና አርብ መስከረም 9 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት በአካል በቃሊቲ ወደብና ተርሚናል እና በሞጆ ሎጀስቲከስ ማዕከል የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ማስረጃ በማሳየት መመልከት ይችላሉ፡፡
ጨረታው አርብ መስከረም 9 ቀን 2018ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከሰዓት 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በክፍል ሁለት ላይ በሚፈልጉት የንብረት አይነት ላይ የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ተእታ ጨምሮ በመሙላት እና ለሚወዳደሩበት የንብረት አይነት የተቀመጠውን 20% (ሃያ በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክበተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /C.P. O በተቋሙ ትክከለኛ ስም የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲከስ (Ethiopian Shipping & logistics) በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
በጨረታ መከፈቻው ሰዓት፤ እለትና ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመክፈት አይታገድም።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549304/0951414204 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ
