Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline29 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Securityየጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን በየሎቱ ይለያያል።
  • opening date2025-09-29 00:00:00
  • Categories Cleaning & Janitorial , Printing And Publishing , Stationery Materials , Printer And Photocopy Machine

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም-

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  • በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
  • የንግድ ምዝገባ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
  • የቫት ሰርተፍኬት
  • በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ

ሎት1. የጽህፈት መሳርያዎችና የተለያየ ሞዴል ያላቸዉ ፕሪንተሮች ቶነር የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር--25,000.00(ሀያ አምስት ሺህ ብር)

ሎት 2. የጽዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር———16,059.02(አስራ ስድስት ሺህ ሃምሳ ዘጠኝ ብር ከo2/100 ሳ)

ሎት 3. የህትመት አገልግሎት ስራዎች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር——— 25,000.00(ሃያ አምስት ሺህ ብር)

  • ከላይ በዝርዝር በቀረበው መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚሹ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የድጋፍ ደብዳቤ የጨረታ ሰነዱን በነጻ እንዲወስዱ ያስችላቸዋል።
  • የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበርያ በተናጠል በሲ.ፒ.ኦ፣ ቢድቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየር ላይከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምርያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ እና ቅጂ በሚል በጉልህ በሚታይመልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበርያ ቴክኒከ ዋና ሰነድ ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መገኘት አለበት፡፡
  • ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

 

  • ለሎት 1 እና ሎት 2 ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ለእያንዳንዱ ሳምፕል መቅረብ ያለበት ሲሆን ሳምፕል ያልቀረበበት ዕቃ ለውድድር አይቀርብም። ሆኖም ግን ሎት 3 ሳምፕል በድርጅታችን የሚቀርብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  • ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነባሩ ህንጻ ምድር ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም። የጨረታ መከፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  • ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

የኢትዮጲያ ፕሬስ ድርጅት

Save Tender