የትራንስፖርት አገልግሎት ግዢ የጨረታ ቁጥር፡- GN-006/2018 በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለአዘዞ-ጎንደር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚሆን ብዛቱ ከ8,000 እስከ 15,000 የሚደርስ ኩንታል ሲሚንቶ ከናሽናል ሲሚንቶ ለሚ ፕላንት ወደ ጐንደር ከተማ በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
የብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የትራንስፖርት አገልግሎት ግዢ የጨረታ ቁጥር፡- GN-006/2018 በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለአዘዞ-ጎንደር መንገድ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚሆን ብዛቱ ከ8,000 እስከ 15,000 የሚደርስ ኩንታል ሲሚንቶ ከናሽናል ሲሚንቶ ለሚ ፕላንት ወደ ጐንደር ከተማ በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና የንግድ ምዝገባ ፈቃዳቸው በቂ የጭነት ትራንስፖርት አቅም ያላቸው ስለመሆኑ የሚያረጋግጥ (የመልካም ሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ) ድርጅቶች ለዚህ ጨረታ ሲባል የተዘጋጀውን ሰነድ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እቃ ግዥ ቡድን 1 እና ቡድን 2 ቢሮ ወይንም ጎንደር ከሚገኘው የዲስትሪክቱ ጽ/ቤት በነፃ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን ከ15ኛው ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በ4፡00 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር እቃ ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09-11-66-49-88/ 09-25-35-68-90 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጎንደር መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
