በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት መስተዳድር ድርጅታችን የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018ዓ.ም የበጀት ዓመት ለድርጅቱ ሥራ የሚያገለግሉ።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት መስተዳድር ድርጅታችን የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2018ዓ.ም የበጀት ዓመት ለድርጅቱ ሥራ የሚያገለግሉ።
Lot.1 ቱቡላሬ ብረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1. ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃዳቸውን ያላቸው::
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (VAT) ያላቸው::
3 በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት /7/ ተከታታይ የስራ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላል፡፡
5. ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 1% በተረጋገጠ ባንክ (CPO) በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
6. ተጫራቶች የሚጫረቱበትን የእቃውን ስፔሲፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመፃፍና ዕታው ላይም በግልፅ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
7 ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰባት /7/ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ጠብቆ ሰባት /7/ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዚያው ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በእለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
10. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክከል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡
11. ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረግ እና መሰረዝ (Material Devation) አይቻልም።
12. ከሎት ውስጥ ከተሰጡት ዕቃዎች ዝርዝር በከፊል መወዳደር (Partial Offer) አይቻልም፡፡
13. ተጫራቾች በድርጅቱ በዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም (የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የሚል ማህተም) ባረፈበት ላይ ብቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም፡፡
14. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-437-16-83 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
የቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1ኛ ደረጃ የመጠጥ ውሃ እና
ፍሳሽ አገልገሱት ደርጅት
