Tender Detail

Tender Details


የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ለ2018 በጀት ዓመት ለዋና ጽ/ቤትና ለገቢ ማመንጫ ማዕከላት ለሥራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ-

Hawassa University (ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ)


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

  1. የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ለ2018 በጀት ዓመት ለዋና ጽ/ቤትና ለገቢ ማመንጫ ማዕከላት ለሥራ አገልግሎት ላይ የሚውሉ-

ሎት 1፡- የእንስሳት መኖ ለማቀነባበር የሚሆን እህልና ጥራጥሬ

ሎት 2፡- ለእንጨትና ብረታ ብረት ወርክ ሾፕ ለሥራ አገልግሎት የሚሆኑ የፋብሪካ ውጤቶች

ሎት 3፡- ለቢሮ ሥራ አገልግሎት የሚሆን የጽህፈት መሳሪያዎች

ሎት 4፡- የዶሮ ኬጅ እድሳትና ጥገና

ሎት 5፡- የተለያዩ ወርከሾፕ ማሽነሪዎች እድሳትና ጥገና

ሎት 6፡- ለድለባ አገልግሎት የሚሆን ቁም ከብቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት አለበት።

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድና የንግድ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የታክስ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚኖሩት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከታች የተቀመጠውን አድራሻ በመጠቀም ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለሎት 1 እስከ 3 ለእያንዳንዳቸው የጨረታውን ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) እና ለሎት 4፣ 5 እና ሎት 6 የጨረታውን ማስከበሪያ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት አስራ አምስተኛ ቀን 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በህዝብ በዓላትና የእረፍት ቀን ከዋለ ቀጣይ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  5. የጨረታ ውድድር ሂደት እንደተጠናቀቀ ውጤቱ በኢንተርፕራይዙ በኩል ለተወዳዳሪዎች ባስመዘገቡት አድራሻ አማካይነት ይገለጽላቸዋል።
  6. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ፖሊሲና ልማት ሕንፃ ወይም ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በሚገኝበት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ

* ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር /0462122858 /0924388128 /ደውሎ መጠየቅ ይቻላሉ፡፡

 

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

 

Save Tender