የሽመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተገለፁትን ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 የደንብ ልብሶች፣ ሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች፣ ሎት 5 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 6 የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ ሎት 7 የላብራቶሪ እቃዎች እና የማስተማሪያ ኬሚካሎች፣ ሎት 8 የተማሪዎች አጋዥ መጻሕፍቶች፣ ሎት 9 ምንጣፍ እና መጋረጃ፣ ሎት 10 ለሕፃናት ማቆያ ከፍል የሚሆኑ የተለያዩ መጫወቻ እቃዎች እና ሎት 11 የኤሌክትሪከ እቃዎች እና የሕንፃ ማሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክ/ከተማ የሽመልስ ሃብቴ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር፡- 01/2018
የሽመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተገለፁትን ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 2 የፅዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 የደንብ ልብሶች፣ ሎት 4 የስፖርት ዕቃዎች፣ ሎት 5 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት 6 የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣ ሎት 7 የላብራቶሪ እቃዎች እና የማስተማሪያ ኬሚካሎች፣ ሎት 8 የተማሪዎች አጋዥ መጻሕፍቶች፣ ሎት 9 ምንጣፍ እና መጋረጃ፣ ሎት 10 ለሕፃናት ማቆያ ከፍል የሚሆኑ የተለያዩ መጫወቻ እቃዎች እና ሎት 11 የኤሌክትሪከ እቃዎች እና የሕንፃ ማሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች፡-
1. በተጠቀሰው የሥራ ዘርፍ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃዎችን ኦሪጅናል እና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ብር 8,000 ማስያዝ የሚችሉ ሲሆን CPO ኦርጅናል ሰነድ የታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ መካተት ይኖርበታል፡፡
4. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ዕቃ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
5.ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ1ዐ ተከታታይ የሥራ ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ በላይኛው ግቢ በት/ቤቱ ሂሣብ ክፍል ቢሮ ቁጥር 2 ሁለት በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች ሰነዱ ላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የሚሸጥበትን ዋጋ 15 % ቫትን ጨምሮ በመሙላት እና ሌሎች ማስረጃዎችን በማህተም በማረጋገጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እስከ 10 ቀናት በ11፡30 ሰዓት ድረስ በዚሁ በታሽገው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
8. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ከ7ኛው /ከሰባተኛው ቀን ቀጥሎ ውል መፈፀምና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ ከተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ አለባቸው፡፡
9. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ:- ገነት ሆቴል ጀርባ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያ የሽመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
