የካራአሎ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
የካራአሎ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
ግልጽ የግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2017 ዓ.ም
የካራአሎ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1ኛ. 6211 የደንብ ልብስ ሲፒኦ 35,000.00.
2ኛ. 6212 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሲፒኦ 30,000.00
3ኛ. 6213 የተለያዩ የህትመት ስራዎች ሲፒኦ 32,600
4ኛ. 6214 አላቂ የህከምና ዕቃዎች 4000
5ኛ .6215 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ሲፒኦ 35,000
6ኛ 6218 የጽዳት ዕቃዎች ሲፒኦ 35,000
7ኛ 6314 ቋሚ የቢሮ ዕቃ ለህንጻ ቁሳቁስ 20,000
8ኛ 6219 የተለያዩ የስፖርት መርጃ መሳሪያዎች 6,000
9ኛ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች እና የልብስ ስፌት 3000
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባችሁ፡-
1. በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስከርወረቀት፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ የከፋይነት ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የሚያቀርቡት ሰነድ ኮፒ ለእይታ የማያስቸግር ግልፅ መሆን ይኖርበታል።
2. የንግድ ስራ ፈቃድ መስክ ከጀርባ ይመልከቱ የሚለውን ኮፒ ጨምሮ ማቅረብ የሚችሉ።
3.ህጋዊ የካሽ ሬጂስተር ማሽን ደረሰኝ ወይም ህጋዊ በገቢዎች ፈቃድ የታተመ የእጅ በእጅ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ባገኙበት መስከ ላይብቻ ይሆናል፡፡
5. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) በመከፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በት/ቤቱ ግዥ ከፍል መውሰድ ይኖርባቸዋል።
6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ከላይ በየሎቱ በተዘረዘረው መሰረት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7.ተጫራቾች ያሸነፋበትን ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በግልጽ በመጻፍ እና ማህተም በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በስራ ሰዓት በግዥ ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. የዕቃውን ዋጋ ሲሞሉ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ቫትን ጨምሮ መሙላት፣ ሰነዱ ላይ የስራ አስኪያጁ ፊርማ እና ማህተም ማረፍ አለበት፡፡
10. ተጫራቾች ለሚሠዳደሩበት ዕቃ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በንብረት ከፍል ማስገባት እና ተወዳድረው ባሸነፋበት ዕቃ ላይ ከናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው ማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ ከሆነ መልሰው ትከክለኛውን ቀይረው የማምጣት ግዴታ አለባቸው።
11. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ከወጣበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4:30 ላይ የሚከፈት ይሆናል።
12. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ስትመልሱ ሙሉ አድራሻችሁን በተሰጠው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በትክክል መሙላት ይኖርባችኋል።
13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ወይም በከፈል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ የካ/ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታ ኮተቤ መሳለሚያ ዋርካ ትምህርት ቤት አጠገብ ካራአሎ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ሲሆን
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0116-681280/0116-600470
14. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ቢበዛ ለ60 ቀናት ብቻ ነው፡፡
የካራአሎ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
