Tender Detail

Tender Details

  • Company DEBRE MARKOS COMPREHENSIVE SPECIALIZED HOSPITAL (ደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)
  • Address ደብረ ማርቆስ : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 058 771 22 46
  • Website
  • Deadline19 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security3000.00 /ሶስት ሺህ ብር/
  • opening date2025-09-19 00:00:00
  • Categories Vehicle

የደ/ማ/አጠ/ስፔ/ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ ሠራተኞች አገልግሎት የሚውሉ 60 እና ከዚያ በላይ ወንበር ያለው 1ኛ ደረጃ አውቶቢስ እና የሸንት ቤት ቆሻሻ ማስወገጃ ቦቲ መኪና ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል።

DEBRE MARKOS COMPREHENSIVE SPECIALIZED HOSPITAL (ደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደ/ማ/አጠ/ስፔ/ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ ሠራተኞች አገልግሎት የሚውሉ 60 እና ከዚያ በላይ ወንበር ያለው 1ኛ ደረጃ አውቶቢስ እና የሸንት ቤት ቆሻሻ ማስወገጃ ቦቲ መኪና ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል።

ስለሆነም፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ያላቸው።
  2. በዚህ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ ብቻ መሆን አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / ቢድ ቦንድ / ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000.00 በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / ሲፒኦ/ ኦርጅናሉን ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ የደረሰኞችን ፎቶ ኮፒ ከፋይናንስ ወይም ከዋጋ ማቅረቢያ ፖስታ ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ጨረታው 15 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 4፡00 ታሽጎ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል።
  5. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ማ/አጠ/ስፔ/ሆስፒታል የእስተዳደር ህንፃ ላይ ይካሄዳል ፡፡
  7. የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
  8. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን አንስቶ የሚቆጠር ዝቅተኛ ቀን ከ40 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
  11. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  12. ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከግ/ፋ/ ን አ/ደ/የስ/ሂደት በአካል በመገኘት / በስልክ ቁጥር 058 771 22 46 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

ደብረ ማርቆስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

 

Save Tender