Tender Detail

Tender Details

  • Company በደቡብ ኢ/ክ/ መንግሥት በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ጎፋ ዞን ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: - - - - - -
  • Website
  • Deadline19 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security5000.00 /አምስት ሺህ ብር/
  • opening date2025-09-19 00:00:00
  • Categories Stationery Materials , Electronics Materials

በደቡብ ኢ/ክ/ መንግሥት በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክትር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስና የጽህፈት መሣሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በደቡብ ኢ/ክ/ መንግሥት በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

1ኛ ዙር ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢ/ክ/ መንግሥት በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክትር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በ2018 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስና የጽህፈት መሣሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የተጫራቾች መስፈርቶች፡-

  1. በዘርፉ በ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
  3. የዘርፉ ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  4. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  5. በመንግስት ግዥ አቅራቢነት የተመዘገበ፣
  6. የግዥ ኤጀንሲ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ዕገዳ ያልተጣለበት፣

የተጫራቾች ግዲታዎች፡-

  1. ከተራ ቁጥር 1 እስክ 6 ያሉ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብርና ሰነድ በመግዛት ለዚህ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  2. ጨረታውን ያሽነፈው ድርጅት ዕቃ በራሱ ወጪ እስከ ደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግቢ ማቅረብ አለበት፣
  3. ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ዕቃ ማቅረብ አለበት፣
  4. ናሙና የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ለመ/ቤቱ በቅድሚያ ማቅረብ አለበት
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ እውቅና ካለው ባንክ ማስያዝ አለበት፡፡
  6. የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ የግዥ ዋጋ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም የባንክ cpo ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  7. ለአሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል ማግባት አለበት፡፡
  8. የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
  9. የጨረታ ሰነድ ከደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመግዛት የገዙትን ሰነድ በመሙላት የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት ዋናውና ኮፒው በሁለት ለብቻ አሽጎ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የሥራ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛውን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ የሚከፈተው ከታሸገበት 30 ደቂቃ በኋላ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሰነድ የመክፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
  2. መ/ቤቱ ሌላ የተሻለ ለማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  3. ማንኛውም ተጫራች የሚፈልገውን ዕቃ ዋጋ የማቅረቢያ ሰነድ የተጠቀሰውን ዕቃ ሙሉ በሙሉ መሙላት።

 

በደቡብ ኢ/ክ/ መንግሥት በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender