የጨረታ መሰያ ቁጥር 01/2018 በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት ላይየሚከተሉትን ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ
የአንደኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መሰያ ቁጥር 01/2018
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴከኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት ላይየሚከተሉትን ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል፡-
1. ሎት-01 የኮንስትራክሽን የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ
2. ሎት - 02 የሰርቬይንግ የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ
3. ሎት -03 የአዉቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ
4. ሎት - 04 የማኑፋክቸሪንግ ሥልጠና ዕቃዎች ግዢ
5. ሎት - 05 የኤሌክትሪካል ኤሌከትሮኒክስ የሥልጠና ዕቃዎች ግዥ
6. ሎት-06 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ
7. ሎት -07 የጽሕፈት መሣሪያዎች (STAIONERY MATERIALS)
8. ሎት - 08 የጽዳት እቃዎች ግዢ
9. ሎት - 09 የሴፍቲ ማቴሪያል የሥልጠና እቃዎች ግዥ
በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ መወዳደር ለሚትፈልጉ ተጫራቾች-
1. በዘርፉ ህጋዊ የሆነና የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የምስክርወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና በተወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የአቅራቢነት ሰርትፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠና በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የእቃ አቅራቢነት ማስረጃ(ደብዳቤ) ማቅረብ አለባቸው።
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN No) የሚገልፁ የምስክር ወረቀት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች የሚጫረቱበት የእቃዎች ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በሚታይ መልኩ ያለስርዝ ድልዝ በመሙላት የሞሉት ዋጋ በኢትዮጵያ ብር ሆኖ ከቫት በፊት ያለው ዋጋ መሆን አለበት።
6. ተጫራቾች በገዙት ጨረታ ሰነድ በሁሉም ገፅ ላይ የድርጅቱ ባለቤት ፊርማ ሙሉ አድራሻውንና ህጋዊ ማህተም ያረፈበት ኦሪጅናሉን እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ለእያንዳንዱ ምድብ(ሎት) ከባንክ በተረጋገጠ CPO 10,000.00(አስር ሺህ) ብር ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገበት አለባቸው::
8. ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንከ አካውንት ቁጥራቸውን የሚገልፅ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ የግዥ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል። በጨረታው መከፈቻ ቀንና ሰዓት ተጫራቾችም ሆኑ ህጋዊ ወኪሎቻው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
11. የጨረታ መከፈቻው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይተዘግቶ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
12. ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።
13. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ስተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0251-13 09 52/53/54/55
ፖስታ ሳጥን ቁጥር 2601
ፋክስ ቁጥር 0251-12 45 53 ማግኘት ይችሳሱ።
ተጨማሪ ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ የሚሞሉት ዋጋ ከቫት በፊት መሆኑን እንዳይረሱት በድጋሚ ማሳሰብ እንፈልጋለን፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ--ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
