Tender Detail

Tender Details


በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ትም/ፅ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁ-2 ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ት/ቤቶች ጽ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2018

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ትም/ፅ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁ-2 ት/ቤት ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1. የደንብ ልብስ .

ሎት 2. የፅህፈት መሣሪያዎች

ሎት 3. ህትመት

ሎት 4. የትምህርት መሣሪያዎች

ሎት 5. የፅዳት መመሣሪያዎች

ሎት 6. ለማሽነሪ እና ለተገጣጣሚ ቋሚ

ሎት 7 እድሳት እና ጥገና አገልግሎት

በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

1. የታደሰ የዘርፉን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡

2. የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

3. የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

4. ተጫራቾች የግዥና ንብረት ማስወገድ ባለስልጣን ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝርማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

5. ተጫራቾች የመንግስት ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን የሚገልፅ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡

6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይየስራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጄ/ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁ-2 ት/ቤት ግዥ ከፍል በመቅረብ ከሎት 1 እስከ ሎት 7 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሎት ቁጥር 1 ሰላሳ ሽህ ብር ብቻ (30,000) ሎት2 ሀያ ሽህ ብር ብቻ (20,000) ሎት 3, ሶስት ሽህ ብር ብቻ (3,000) ሎት4 ስምንት ሽህ(8,000) ሎት 5, ሰላሳ አምስት ሽህ ብር ብቻ (35,000) ሎት 6 ሃያ ሽህ ብር ብቻ (20,000) እና ሎት 7ሶስት ሽህ ብር ብቻ (3,000) ብር ሲሆን በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁ-2 ት/ቤት ስም አዘጋጅቶ ማቅረብ የሚችል፡፡

 

8. በሽርክና ማህበር ተደራጅቶ የሚሰሩ አቅራቢዎች የተጠየቀውን ዋስትና የሚያቀርቡት ደብዳቤ ከአደራጃቸው አካል በት/ ቤቱ አድራሻ ማቅረብ የሚችል፡፡

9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ይታሸጋል በዕለቱ የስራ ሰዓት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቦታ ይከፈታል፡፡

10. ተጫራቾች በሙሉ በሚወዳደሩበት ሎት ላይ ጨረታው ከመከፈቱ 1 ቀን ቀደም ብሎ በት/ቤቱ ግዥ ከፍል ናሙና ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

11. ተጫራቾች በገዙት ጨረታ ሰነድ ባለው የዋጋ መሙያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምሮ በግልጽ ሞልቶ በማህተም አስደግፎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

12. ተጫራቾች በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ 7 ተከታታይበስራ ቀናት ውስጥ ቀርበው ከአሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ 5% የውል ማስከበሪያ በት/ቤቱ ስም በቼክ በሲፒኦ ለግዥ ክፍል በማቅረብ ውል መግባት አለባቸው፡፡ ያስያዙትን ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡና ውሉን ተመላሽ ሲያደርጉ ነው፡፡

13. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

14. ዕቃውን ሲያስገቡ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ሲሆን ከሰዓት ደግሞ 7፡00 ሰዓት እስከ 9፡00 ድረስ መሆኑን እያሳውቅን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ የሚመጡ ከሆነ የማናስተናግዳቸው መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አድራሻ፣ አ.አ ኮ ቀ/ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ጄ/ዋ/ጉ/1ኛ ደ/ቁ-2 ት/ቤት አለም ባንከ እሳት አደጋ ፊት ለፊት

ለተጨማሪ መረጃ ስልከ ቁጥሮች 0912255229/0910190376

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍል ከተማ ወረዳ 07 ትም/ፅ/ቤት የጄኔራል ዋቆ ጉቱ 1ኛ ደረጃ ቁ-2 ት/ቤት

Save Tender