Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን
  • Address አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0910006953
  • Website
  • Deadline09 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-09-09 00:00:00
  • Categories Electronics Materials , Kitchen Materials

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የአበያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ዘላቂ የደን ልማትና ጥበቃ ፕሮጀክት አሰላ ከተማ ለሚገኘው አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራ አንድ የዳቦ መጋገሪያ ማሽንና ተያያዢነት ያላቸውን መገልገያ መሳሪያዎችን ጨምሮ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን


 

የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ግዢ ጨረታ

 

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የአበያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ዘላቂ የደን ልማትና ጥበቃ ፕሮጀክት አሰላ ከተማ ለሚገኘው አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠራ አንድ የዳቦ መጋገሪያ ማሽንና ተያያዢነት ያላቸውን መገልገያ መሳሪያዎችን ጨምሮ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የሚፈለገው የዳቦ መጋገሪ ማሽንና ተያያዥ መገልገያዎች ዓይነትና ብዛት የጣሊያን አገር ሥሪት የሆነ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ብዛት 1 /አንድ/

  • ለእያንዳንዱ ክፍል ዲጂታል ሂት ኮንሮለር ያለው 380V 28 kw የሆነ፣
  • ባለ 5 ዴክ 2*5 = 10 ፓትራ ሆኖ በእያንዳንዱ ዴክ ውስጥ 2*60*40 የሚጋግር
  • የፓትራ ስፋት 60.17 ሣ.ሜ. የሆነ
  • የሊጥ ማቡኪያው በአንድ ጊዜ 25 ኪ.ግ. የሚያቦካ
  • ማኮፈሻው ባለ ባለ 20 ፓትራ 60 ሣ.ሜ በ40 ሣ.ሜ. የሆነ
  • 20 የመጋገሪያ ትሪዎች

የተወዳዳሪዎች መስፈርት፤

  1. በአቅራቢነት የሥራ ዘርፍ ለመሠማራት የሚያስችላቸው ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የ2017 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ እንዲሁም ተገቢውን የመንግሥት ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ የግብር ክሊራንስ ማስረጃና በሚመለከተው የመንግሥታዊ ንግድ ተቋም ቢሮ/የተሠጣቸውን የቫት ቲን የምዝገባ ሠርቲፊኬት ማስረጃ ማቅረብ
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አሥር/ ቀናት ውስጥ የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ህጋዊ በሆነ የድርጅታቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /ፕሮፎርማ/ ላይ በማስፈር፤ በድርጅታቸው ማህተምና ፊርማ አረጋግጠውና በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አሰላ ከተማ በሚገኘው የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው።
  3. ጨረታው በአሥረኛው ቀን ከጠዋቱ ልክ 4፡00 ሠዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ መገኘት በፈለጉ ተጫራቾች እና የፕሮጀክቱ ጨረታ ኮሚቴ በተገኙበት ይከፈታል። 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  4. የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጨረታ ኮሚቴም በተጫራቾች የቀረበውንና የጨረታ ሰነድ ላይ የሠፈሩትን የቴክኒክ እና ፋይናንስ ዝርዝሮችን ከገመገመና ካጣራ በኋላ ጨረታው በተከፈተ በሦስተኛው ቀን አሸናፊ የሆነውን ድርጅት በማስታወቂያ እንዲገለጽ ያደርጋል።
  5. የግዢ ጨረታውን አሽናፊ የሆነው ድርጅት ከፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በሚደረገው የስምምነት ውል መሠረት በ8 /ስምንት/ ቀናት ውስጥ ማሽኑንና ተያያዥ መሳሪያዎቹን አሰላ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ድረስ አጓጉዞ ማስረከብና በተጨማሪም ስለ አጠቃላይ የማሽኑ አጠቃቀም በባለሙያ የታገዘ አጭር ሥልጠና መስጠት ይጠበቅበታል።
  6. የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሠረዝ መብት አለው።

ለበለጠ መረጃ:- በስልክ ቁጥር 0913720420 ወይም 0912247019 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የፕሮጀከት ጽ/ቤት አድራሻ፡- ኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፤ አሰሳ ከተማ፤ ቀበሌ 11 ልዩ ቦታው አርዱ፣ ወደ በሚወስደው አስፓልት 30 ሜትር ያህል አልፈው ከሄዱ በኋላ በግራ በኩል የፕሮጀክቱ ጽ/ቤት ጠቋሚ ታፔላን አይተው መምጣት ይችላሉ።

 

Save Tender