Tender Detail

Tender Details


ድርጅታችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ ቀጥሎ የተመለከቱትን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Tsehay Industry S.C. Kaliti Metal Products Factory (ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ)


 

ጨረታ ቁጥር 04/2018

 

ድርጅታችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ ቀጥሎ የተመለከቱትን የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. በሎት 1 የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ወንበሮች፤ ኮምፒውተሮች ፕሪንተሮች፤ ስካነር፤ ላብቶፕ፤ የሰዓት መቆጣጠሪያ መሳሪያ ወዘተ
  2. በሎት 2 የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኬብሎችንና የኤሌክትረክ ዕቃዎችን፤ የቧንቧ ዕቃዎች፤ የፋብሪካ ዎርክ ሾፕ ዕቃዎች (የተለያዩ ኩሽኔቶች፤ የዕቃ ማንሻ ቤልቶች፣ ወዘተ….) የህንጻ ስራ መሳሪያዎች እና መገልገያ ዕቃዎች፤ እና ሌሎችም

ስለሆነም፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. የታደሠ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ማስረጃ በሚመለከተው መ/ቤት የተሰጠ ብቃት ማረጋገጫ ወይም በመንግስት የአቅራቢነት ዝርዝር ኤሌክትሮኒክ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ ከካፍደም ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 700 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ከድርጅቱ የግዢ ዋና ክፍል ለየሎቱ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
  4. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያለው ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመውሰድ በጨረታው የሚወዳደሩበት የፋይናንሺያል ሠነዶቻችውን በታሽገ ፖስታ በማድረግ መስከረም 06 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በፊት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከላይ በተገለፀው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው መስከረም 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ/ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 4 34 03 87 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ

 

Save Tender