Tender Detail

Tender Details

  • Company የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት
  • Address ቢሾፍቱ ከተማ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-437-16-83
  • Website
  • Deadline14 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security1%
  • opening date2025-09-14 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical , Transportation Service And Cargo

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት ለሥራ የሚገለገልበትን፡ Lot.1. Electric Tricycle Lot2 TVS Bajaj በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትይፈልጋል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት


                                                              የጨረታ ማስታወቂያ 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት ለሥራ የሚገለገልበትን፡

 Lot.1. Electric Tricycle 

Lot2 TVS Bajaj በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትይፈልጋል፡፡

የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ 

  1. ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡ 

  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቫት) ያላቸው፡፡ 

  3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስተር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ:: 

  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት /15/ ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በመ/ቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላል፡፡ 

  5. ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 1% በተረጋገጠ ባንክ (CPO) በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡ 

  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃውን ስፔስፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመጻፍና ዕቃው ላይም በግልፅ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡ 

  7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡ 

  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በስም በታሸገ ኤንቬሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ በ15ኛው ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

  9. የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ተከታታይ ቀናት ጠብቆ በ15ኛው ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ጨረታው ተዘግቶ በዛው ቀን 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ እለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡ 

  10. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡ 

  11. ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረገ እና መሰረዝ (Material Devation) አይቻልም፡፡

  12. ተጫራቾች በድርጅቱ በዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም (የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የሚል ማህተም) ባረፈበተ ላይ ብቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላችውም፡፡ 

  13. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

  14. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡- 011-437-16-83 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ 

                                                           የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት

Save Tender