ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ሎት1.የጽህፈት መሳሪያ ሎት 2. የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ሎት 3. የተዘጋጁ ልብሶች ሎት 4. ቆዳ ጫማ ሎት 5. ፕላስቲከ ቦት ጫማ ሎት 6. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 7. የፈርኒቸር እቃዎች ሎት 8. የመኪና እቃ ሎት 9. የጽዳት እቃ ሎት 10. አነስተኛ ቋሚ እቃ ሎት 11. የስፖርት ትጥቅ ሎት12. ህትመት ሎት13. የመኪና ጎማ ሎት14. የመኪና ዘይትና ቅባት ሎት15. የሞተር ሳይክል ጥገና ሎት16. የኤሌከትሮኒክስ ጥገና ሎት17.የውሃ ከሎሪን ሎት19.የቢሮ መጋረጃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ሎት1.የጽህፈት መሳሪያ ሎት 2. የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ ሎት 3. የተዘጋጁ ልብሶች ሎት 4. ቆዳ ጫማ ሎት 5. ፕላስቲከ ቦት ጫማ ሎት 6. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 7. የፈርኒቸር እቃዎች ሎት 8. የመኪና እቃ ሎት 9. የጽዳት እቃ ሎት 10. አነስተኛ ቋሚ እቃ ሎት 11. የስፖርት ትጥቅ ሎት12. ህትመት ሎት13. የመኪና ጎማ ሎት14. የመኪና ዘይትና ቅባት ሎት15. የሞተር ሳይክል ጥገና ሎት16. የኤሌከትሮኒክስ ጥገና ሎት17.የውሃ ክሎሪን ሎት19.የቢሮ መጋረጃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ
1. ተጫራቾች በዘርፉ በዘመኑ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN No /ያላቸው ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፉ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገበ እና ለመመዝገባቸው የምስከር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ ::
2. እቃዎቹን በአንድ ጊዜ በአይነት በመጠን በጥራት ሳያጓድል ማቅረብ የሚችል፡፡
3. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን ማስፈርአለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ የጽ/መሳሪያ 40,000 ብር ለብትን ጨርቅ 6,000 ብር ለተዘጋጁ ልብሶች 8,000 ብር ለቆዳ ጫማ 10,000 ብር ለፕላስቲክ ቦት ጫማ 1,000 ብር ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 2000 ብር ለፈርኒቸር 36,000 ብር የመኪና እቃዎች 30,000 ብር ለጽዳት እቃ 6,000 ብር ለአነስተኛ ቋሚ እቃዎች 4,000 ብር የስፖርት ትጥቅ 2,000 ብር ለህትመት 1,000 ብር የመኪና ጎማ 12,000 ብር የመኪና ዘይት እና ቅባት 20,000 የሞተር ሳይክል ጥገና 2,000 የኤሌከትሮኒክስ ጥገና 2,000 ብር የውሃ ከሎሪን 3,000 ብር የቢሮ መጋረጃ 4,600 ብር በባንክ በተመሰከረለት ሲፒአ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንከ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ገ/ዋና ጽ/ቤት በመሂı ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት የእቃ ግዥው መ/ቤቱን የተጫራቾችን ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም የግዥውን አይነት በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
6. ጨረታው በዚሁ እለት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ይታሸግና በእለቱ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል ፡
7. 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግስት የሥራ ቀን ይከፈታል፤
8. መ/ቤቱ ጨረታውን በሎት ያወዳድራል፡፡
9. ተጫራቾች የእቃውን አይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይንም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት ከሎት ማጉደል አይችሉም፡፡
10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት አን/ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ጫጫ ከተማ ድረስ በየንብረት ከፍሉ ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
11.ከአንድ ጨረታ በላይ የሚወዳደሩ ከሆነ የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ በተናጠል በየሎቱ ለየብቻው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
12. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ በሚሆኑበት ጊዜ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ውል ከመግባቱ በፊት ናሙና ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
13. በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦርጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝርስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
14. በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 20,000/ሃያ ሺህ/ እና ለአገልግሎት ከብር 10,000/አስር ሺህ/በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ከፍያ ላይ 3% ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀርይሆናል፡፡
15. ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግና በፍሉድ መደለዝ አይፈቀድም ፡፡ ምንአልባት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ ስህተት ቢፈጠር አንድ ሰረዝ አድርጐ ስለመሰረዙ መፈረም አለበት፡፡
16. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
17. ጽ/ቤቱ የሚገኝው ከአ/አበባ በስተ ሰሜን n0 ኪ/ሜ ርቀት በደብረ ብርሃን መስመር ላይ ነው፡፡
18. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-632-01-47 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን የአንጎለላና በሳና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
