ሀና ቅ/አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮና የትምህርት እቃዎችን፥ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ጥገና እና ህትመት ስራዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሀና ቅ/አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 001
ሀና ቅ/አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ የቢሮና የትምህርት እቃዎችን፥ የደንብ ልብስ፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ጥገና እና ህትመት ስራዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡በጨረታው ለመወዳደርየምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል::
1. በዘርፉ የተሰማሩ የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የታከስ ከፋይነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣በእቅራቢዎች ዝርዝርየተመዘገቡ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የገቢዎች ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
|
ሎት |
የእቃው/አገልግሎት አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት1 |
የፅህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች |
20,000.00 |
|
ሎት2 |
የደንብ ልብስ |
25,000.00 |
|
ሎት3 |
የዕዳት እቃዎች |
27,000.00 |
|
ሎት4 |
የትምህርት እቃዎች |
3,000.00 |
|
ሎት5 |
ቃሚ እቃዎች |
11,000.00 |
|
ሎት6 |
የጥገና ዕቃዎች |
7,000.00 |
|
ሎት7 |
የህትመት ስራዎች |
2,000.00 |
2. ተጫራቾች ከዚህ በላይ በሠንጠረዥ በተመለከተው መሰረት በሚወዳደሩበት ሎት ፊት በፊት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ሀና ቅ/አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በየሎቱ የማይመለስ ብር 150/አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመከፈል ከት/ቤቱ ፋይናንስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በን/ስ/ላ/ከ/ከ ወረዳ 14 ልዩ ስሙ ሰፈራ ሀና ቅ/አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 003 በመምጣት የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላል::
4. ጥቃቅን እና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች አምራች በሆኑበት ዘርፍ ላይ ብቻ ሰነዱን በነፃ መውሰድ ይችላሉ::
5. ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋውን ከነቫቱ ሞልተውና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የጨረታ ሰነዱ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በዓል ካልሆነ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾ ወይም ህጋዊ ተወካያቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ጨረታ ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን በግልፅ ለይቶ በመፃፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል እንዲሁም ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መቅረብ አለበት፡፡
8. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: አድራሻ፡- ን/ስ/ላ/ከ/ከ/ወረዳ 14 ሰፈራ ታክሲ ተራ ፊት ለፊት ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 011 8 29 01 64 / 011 8 29 01 65
በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 14 ሀና ቅ/አንደኛ አንደኛና እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
