የአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት አመት የተለያዩ በሎት ምድብ የተከፋፈሉ አጠቃላይ እቃዎች እና የጥገና ስራዎች ማለትም ሎት 1. የደንብ (የስራ ልብስ) ሎት2. አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት3. የህትመት ሎት 4. አላቂ የህከምና እቃዎች ሎት 5. አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት 6. አላቂ የጽዳት እቃዎች ሎት 7. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ሎት8. ለፕላንት ማሸነሪ መሳሪያዎች መግዣ ሎት9. ለህንፃ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ እቃዎችና ሎት1ዐ. የተለያዩ ለፕላንት ማሸነሪ ጥገና እንዲሁም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ት/ቤቱ መግዛት እና ማስጠገን ይፈልጋል፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ትምህርት ቢሮ የአፍሪካ አንድነት ቁ1 አፀደ ሕፃናት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
የመጀመሪያ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር አፍ/አን/ቁ.2/አጸ/ህጻ/የመ/ደ/ት/ቤት/01/2018 ዓ.ም
የአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት አመት የተለያዩ በሎት ምድብ የተከፋፈሉ አጠቃላይ እቃዎች እና የጥገና ስራዎች ማለትም ሎት 1. የደንብ (የስራ ልብስ) ሎት2. አላቂ የቢሮ እቃዎች ሎት3. የህትመት ሎት 4. አላቂ የህከምና እቃዎች ሎት 5. አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት 6. አላቂ የጽዳት እቃዎች ሎት 7. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ሎት8. ለፕላንት ማሸነሪ መሳሪያዎች መግዣ ሎት9. ለህንፃ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ እቃዎችና ሎት1ዐ. የተለያዩ ለፕላንት ማሸነሪ ጥገና እንዲሁም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ት/ቤቱ መግዛት እና ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል።
1. በዘርፉ የተሰማሩና ጊዜው ያላለፈበት የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ተመዘጋቢ ስለመሆናቸው እንዲሁም ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝርሰነዶችን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2.በመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3.ከላይ በሎት ምድብ የተጠቀሱትን እቃዎች ዝርዝር የተካተተበት የግዥ የግልጽ ጨረታ መመሪያን የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በት/ቤት ውስጥ በሚገኘው የካሸር ቢሮ ቁጥር 4 በመግዛት መውሰድ ይችላሉ ። እንዲሁም ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ካደራጃችሁ አካል የምታመጡት ደበብዳቤ በምን ዘርፍ እንደተደራጃችሁ የሚገልጽ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባችኋል።
4.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግል የሚወዳደሩበትን የእቃዎች ማለትም ለሎት 1. 10000 ብር ለሎት 2. 15000 ብር ለሎት 3. 3000 ብር ለሎት 4. 5000 ብር ለሎት 5. 7000 ብር ለሎት 6, 20000 ብር ሎት 7. 6000 ብር ሎት 8. 5000 ብር ሎት 9. 6000 ብርሎት 10. 10000 ብር በት/ቤቱ ስም ከታወቀ ባንከ የተዘጋጀ ሲፒኦ በማስያዝ ማረጋገጫውን ከሚወዳደሩበት ሰነዶች ጋር ማስገባት ይኖርባችኋል።
5. እንዲሁም የጨረታው አሸናፊ ከሆኑ ደግሞ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ለውል ማስከበሪያ የጠቅላላው የሚያሸናፉትን ዋጋ የሚሆን 10% ውል ሲዋዋሉ ማስያዝ ይኖርባችኋል።
6.ተጫራቾች ለጨረታ የሚያስፈልጉ ሰነዶች እና የእቃዎችን ዝርዝር ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ውስጥ በከፍል 4 ውስጥ በሚገኘው የዋጋ መሙያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም (ቫት) ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለio ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት በአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ሰነድ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ የሚወዳደሩበትን አጠቃላይ ሰነዶች ላይኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት የድርጅታችሁን ከብ ማህተም በማድረግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባችኋል።
7.ተጫራቾች አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችሉም፡፡
8.ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ለሁሉም እቃዎች የቅርብ ጊዜ ምርት (ጊዜው ያላለፈበት ምርት) ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባችኋል።እንዲሁም ናሙና ለማቅረብ የሚቸገሩባቸውን እቃዎች በፎቶ የተደገፈ ጥራት ያለ ምስል ያለው ፎቶ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባችኋል።
9. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛ የስራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ ከሆነ ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 5፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በት/ቤት ውስጥ በሚገኘው የግዥ ከፍል ውስጥ ይከፈታል።
10.ት/ቤቱ የተሻላ የግዥ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለበለጠ መረጃ የት/ቤቱ አድራሻችን ፡- አበበች ጎበና ህጻናት መርጃ አጠገብ ወይም ዮሐንስ ቤ/ክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው አቤት ሆስፒታል ሲደርሱ ወደ ውስጥ በሚየስገባው ኮብል ስቶን ገባ ብሎ ነው። ለበለጠ መረጃ የት/ቤቱ ስልከ ቁጥር (011-1-57-25-91) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ት/ቤቱ
የአፍሪካ አንድነት ቁ.2 አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
