Tender Detail

Tender Details


የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል ለ2018 በጀት አመት የህክምና መሳሪያ ግዥ እና የህንጻ እድሳት፣ የኤሌትሪክና የጀኔተር ጥገና ለአንድ ጊዜ ብቻ እንዲሁም የህክምና መሳሪያ ጥገና እና ለሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ለአንድ ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል ለ2018 በጀት አመት የህክምና መሳሪያ ግዥ እና የህንጻ እድሳት፣ የኤሌትሪክና የጀኔተር ጥገና ለአንድ ጊዜ ብቻ እንዲሁም የህክምና መሳሪያ ጥገና እና ለሰራተኞች የትራንስፖርት አገልግሎት ለአንድ ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም አግባብነት ያላቸውን ሁሉ ለጨረታው እየጋበዝን፡-

  1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የአቅርቦትና የአገልግሎት አይነት የተዛመደ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን-ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የግዥው ወይም የአገልግሎቱ መጠን ከ200,000.00 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-4 የተገለፁትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው አርጅናል ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከሆስፒታሉ ግዥ ክፍል የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ ብቻ ከኦርጅናሉ የጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፓስታ ሙሉ ስምና አድራሻ ጽፎ ማቅረብ ይኖርበታል በተጨማሪም ኦርጅናል ሰነዱ እና ፎቶ ኮፒ ለብቻው ሙሉ አድራሻው ተጽፎ በጥንቃቄ ታሽጎ መቅረብ አለበት።
  8. የጨረታው ተሳታፊዎች ወይም ህጋው ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በማስታወቂያ በወጣበት በመጨረሻ የስራ ቀን በ16ኛ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ሆስፒታሉ ቫት እና ዊዝሆልድ (3%) ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን፤
  11. ሆስፒታሉ በሚጋብዘው የቴክኒክ ባለሙያ ተረጋግጦ እቃው /አገልግሎቱ/ ገቢ ይሆናል፡፡
  12. ሆስፒታሉ በሚያቀርበው ናሙና እቃ ገቢ ይሆናል፡፡
  13. አስፈላጊ መረጃ መስጠት ከፈለጉ በሆስፒታሉ ስልክ ቁጥር 0331117670 መደወል ይችላሉ፡

 

የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

 

Save Tender