የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት እርሻና ተ/ሀ/ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም ተሽከርካሪዎችን /መኪኖችን/ የሚጠግን ጋራዥ አወዳድሮ ለስድስት ወር የጥገና አገልግሎት ስራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት እርሻና ተ/ሀ/ልማት ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት እርሻና ተ/ሀ/ልማት ቢሮ በ2018 ዓ.ም ተሽከርካሪዎችን /መኪኖችን/ የሚጠግን ጋራዥ አወዳድሮ ለስድስት ወር የጥገና አገልግሎት ስራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ማንኛውም በዚሁ የአገልግሎት ሰጪ ዘርፍ የተሰማራ ህጋዊ ጋራዥ በውድድሩ ላይ እንዲካፈል እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈል ጋራዡ ቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ የ3ኛ ደረጃ እና ከዚያ በላይ የጥገና ብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው፤
- ለዘመኑ የታደሰ የመድህን ዋስትና /ኢንሹራንስ ያላቸው፤
- የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያመለከት የጨረታ ሰነድ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀናት ግዥ ንብረት አስተዳደር ክፍል በቁጥር 02 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል አንድ አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ሁለት ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና ጠቅላላውን በአንድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማጠቃለል በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማካተት አለማካተቱን በፋይናንሻል ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልጽ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 5 (አምስት) ፐርሰንት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና/ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን አልወዳደርም ማለት አይችልም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በሀገር ውስጥ አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ግዥ ፋ/ን/አስ/ዳይሬከቶሬት ግዥ ክፍል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው ግዥ ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት በስልክ ቁጥር 0462212413 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ፡፡
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት እርሻና ተ/ሀ/ልማት ቢሮ
