አምቦ የገ/ሀ/ሥራ ዩኒየን ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ ከተማ በሚገኘው መጋዘኑ ያከማቻቸውን የተለያዩ ዓይነት የጤፍ ምርት (1ኛ ደረጃ ነጭ ጤፍ ብዛት 378.46 ኩንታል፤ 2ኛ ደረጃ ነጭ ጤፍ ብዛት 2,469.98 ኩንታል፤ ሰርገኛ ጤፍ ብዛት 1,350.52 ኩንታል፤ ቀይ ጤፍ ብዛት 517.25 ኩንታል ፤ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
እህል ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
አምቦ የገ/ሀ/ሥራ ዩኒየን ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ ከተማ በሚገኘው መጋዘኑ ያከማቻቸውን የተለያዩ ዓይነት የጤፍ ምርት (1ኛ ደረጃ ነጭ ጤፍ ብዛት 378.46 ኩንታል፤ 2ኛ ደረጃ ነጭ ጤፍ ብዛት 2,469.98 ኩንታል፤ ሰርገኛ ጤፍ ብዛት 1,350.52 ኩንታል፤ ቀይ ጤፍ ብዛት 517.25 ኩንታል ፤ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መሥፈርቶች-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከጨረታ መክፈቻ ቀን በፊት ከዩኒየኑ ገበያ መምሪያ በብር 500 መግዛት ይችላሉ፤
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾቹ የእህሎቹን ሁኔታ በአምቦ በሚገኘው በዩኒያኑ መጋዘን ዘወትር በሥራ ሰዓት ተገኝተው ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በቅድሚያ 5% ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፤ ጨረታው እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ሲመለስላቸው አሸናፊዎች ከእህሉ ግዥ ውስጥ የሚታሰብላቸው ይሆናል፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኋላ በ22ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ጠዋት ታሽጎ በዛው ቀን ጠዋት በ05፡00 ሰዓት ላይ አምቦ ባለው በዩኒየኑ ቢሮ ይከፈታል። 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፤፤
- ተጫራቾች/ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅታቸው የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኙ ተጫራቾች ፊት ጨረታው በዕለቱ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመግዣ ዋጋቸውንና ለጨረታው የተጠየቁትን መረጃዎች በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ በገባው ውል መሰረት ክፍያ አጠናቆ ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል፡፡ አሸናፊው በተሰጠው ቀናት ውስጥ ያላነሳ እንደሆነ ያስያዘው ገንዘብ የማይመለስለት ከመሆኑም በላይ በየቀኑ ለእያንዳንዱ ኩንታል የመጋዘን ኪራይ ብር 0.5 ይከፍላል፡፡
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ እንጂ በከፊል መጫረት አይችልም፡፡
- ጨረታውን ያሸናፈ አሸናፊ ለውል ማስከባርያ ጠቅላላውን ዋጋ 10% የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችል፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0913277160 0112363399 ይደውሉ
የአምቦ የገ/ህ/ሥራ ማኅበራት ዩኒየን ኃ. የተወሰነ
