Tender Detail

Tender Details

  • Company Wolaitta Development Association (የወላይታ ልማት ማህበር)
  • Address አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ዳትስን ሰፈር ወደ ግራ በሚያስገባው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461801191
  • Websitehttps://wolaittada.org.et/
  • Deadline16 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security2% (ሁለት ፐርሰንት)
  • opening date2025-09-16 00:00:00
  • Categories Plastic Raw Materials And Products , Stationery Materials

የወላይታ ልማት ማህበር በLuminos second chance education program" በፕሮጀክቱ ድጋፍ ለሚማሩ ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት-1 የተለያዩ አይነት አላቂ የጽ/መሣሪያዎች እና ሎት 2 ፕላስቲክ ወንበርና ጠረጴዛ በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Wolaitta Development Association (የወላይታ ልማት ማህበር)


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ወልማ 02/2025 እ.ኤ.አ

 

የወላይታ ልማት ማህበር በLuminos second chance education program" በፕሮጀክቱ ድጋፍ ለሚማሩ ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ ሎት-1 የተለያዩ አይነት አላቂ የጽ/መሣሪያዎች እና ሎት 2 ፕላስቲክ ወንበርና ጠረጴዛ በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች አሟልተው መቅረብ ያለባቸው መስፈርቶችና ግዴታዎች፡-

  1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጄንሲ በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
  2. ተጫራቾች ስለመልካም ሥራ አፈፃፀማቸው በተመለከተ ከአሁን በፊት ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረቡባቸው ድርጅቶች የተሰጣቸውን የድጋፍ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋው 2% (ሁለት ፐርሰንት) በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዞ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ ባሉት አሥራ አምስት (15) የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በማህበሩ ሥራ ሰዓት ከወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት እና በአ/አበባ ከተማ ከሚገኘው ከወላይታ ልማት ማህበር አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ወይም የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለብቻ ስምና አድራሻውን በፖስታ (በኤንቨሎፕ) ላይ በትክክል በመጻፍና ማህተም በማድረግ አሽገው በወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት እስከ 15ኛው የሥራ ቀናት እስከ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የጨረታ ሳጥን በ15ኛው ሥራ ቀን ልክ በ9፡00 ሰዓት ታሽጎ (ተዘግቶ) ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮችና ታዛቢዎች በተገኙበት ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት በወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል በይፋ ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ሕጋዊ በበዓል ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  7. በጨረታ አሸናፊ የሆነ ድርጅት የጠቅላላ ዋጋውን 10% (አሥር ፐርሰንት) የውል ማስከበሪያ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሠከረ ሲፒኦ በማቅረብ ውል መፈረም አለበት፡፡ ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ገንዘብ ወይም ሲፒአ ሙሉ በሙሉ ለማህበሩ ውርስ ይደረጋል፡፡
  8. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን በኋላ በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልገባ የጨረታ ዋስትናውን ያስቀጣል፡፡
  9. አንድ ተጫራች የሚያሠራው ሲፒኦ በሕጋዊ ባለመብት ወይም ድርጅት ስም መሆን አለበት፡፡
  10. የጨረታ ሠነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልጽ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አይኖረውም ወይም ከውድድር ውጪ ሊያስደርግ ይችላል፡፡
  11. ማህበሩ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት ከ20-30% እንደአስፈላጊነቱ በመጨመር ወይም በመቀነስ መግዛት ይችላል፡፡
  12. አሸናፊው ተጫራች በሚገባው ውል መሠረት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪና ማጓጓዣ በማምጣ ለማህበሩ ዋና ጽ/ቤት በአድራሻው ያስረክባል፡፡
  13. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

ማሳሰቢያ፡- ልማት ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 0461801191 ወይም 0916833499 /0913446217/ መጠቀም ይችላሉ፡፡

 

የወላይታ ልማት ማህበር

 

Save Tender