Tender Detail

Tender Details


በምሥራቅ በባሌ ዞን ራይቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ቶነሮች፣ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብሶች የመኪና ጎማን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በምሥራቅ በባሌ ዞን ራይቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በምሥራቅ በባሌ ዞን ራይቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ቶነሮች፣ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብሶች የመኪና ጎማን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ቀጥሎ የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩበት ተጓዳኝ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው ያሳደሱና በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ) ብር የያዘ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክየተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች ለሁሉም እቃዎች ኮፒና ኦርጅናል ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታዎች በሰም አሸገው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. አቅራቢው ድርጅት ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ መ/ቤቱ ቀርቦ ውል መፈራረም ይኖርበታል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይየሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 በባሌ ዞን ረይቱ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ስም በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000186109485 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማስገባት ሰነዱን ከቢሮ ቁጥር 01 መወሰድ ይችላሉ፡፡

7. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመኖሩ ጨረታ ሰነድ እንዳይከፈት አይከለከልም ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡

8. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር:- 0913655286/0946943515 ደውለው ይጠይቁ፡፡

በምስራቅ ባሌ ዞን የራይቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender