Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
  • Address ኮተቤ ብረታ ብረት መሣሪያዎች ማምረቻ ፋብሪካ አካባቢ አቢሲንያ ባንክ ኪዳነምህረት ቅርንጫፍ ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-5-57-42-95
  • Websitehttps://www.eep.com.et/?lang=am
  • Deadline10 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security500,000.00
  • opening date2025-09-10 00:00:00
  • Categories Machinery

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል፤

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር /EEP/DS/01/17/

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ንብረቶችን ባሉበት ቦታና ሁኔታ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ለመሸጥ እንደሚከተለው አቅርቧል፤

ሎት-1- መልካ ሰዲ የእንፋሎት ኃ/ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት የመጡ ከፍተኛ መጠን፣ ዓይነትና ዋጋ ያላቸው ዕቃዎችና ማሽነሪዎች፤ ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መልካ ሰዲ ከተማ በፕሮጀከት ጣቢያ ቅጥር ግቢ፤

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፤

ማሳሰቢያ፦ ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በአክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን መስፈርቶቹም ከዚህ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-

1. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆኖ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም የታደሰ መታወቂያ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

2. ስለጨረታው አካሄድ እና ንብረቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ የአከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ በነጻ አውርደው መመልከት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ከሰባተኛው ቀን ጀምሮ አክሽን ኢትዮጵያ አከሲዮን ማኅበር ጋርቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት የተቋሙ ጣቢያዎች በመገኘት መመልከት ይቻላል፤

4. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. ተወዳዳሪዎች በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሠራት ወይም ደግሞ በኦንላይን አከሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

7. ጨረታው ከ20/12/2017 እስከ 5/13/2017 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡00 ድረስ ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎች የጨረታውን ሂደት በቀጥታ (online) መከታተል ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የአከሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም (auction.et) ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።

9. በጨረታው አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ለወደፊት አሸናፊነታችሁ በሚገለፅላችሁ ቀን ጀምሮ የሚቆጠር አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉችሁበትን ዋጋ ሙሉውን ከፍያ ለወደፊት በምናሳውቃችሁ በተቋማችን ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ የሽያጭ ውል ስምምነት መፈጸም ግዴታ ይኖርባችኋል፤ ሆኖም ግዴታቸውን የማይወጡ ተጫራቾች ለወድድር ያስያዛችሁት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ. ለተቋማችን ገቢ ይደረጋል፤

10. ከላይ የተጠቀሰውን እና በጨረታ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ መመሪያዎችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ/ሊሰረዝ ይችላል፤

11. ተቋሙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

12. የእከሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር 09-05-11-5511/011-66-68-828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

13. ንብረቶቹን በተመለከተ በስልከ ቁጥር 011-558-14-24 ወይም 011-558-06-49 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

Save Tender