Tender Detail

Tender Details

  • Deadline11 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid Security2%
  • opening date2025-09-11 00:00:00
  • Categories Spare Parts , Vehicle tire

በአብክመ የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ሴከተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት በያዘው የግዥ ዕቅድ መሰረት ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፤ ሎት 2 የመኪና ጎማዎች እና ሎት 3 ለስፖርት ምከር ቤት የስፖርት ትጥቅ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት ሴከተር መ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት በያዘው የግዥ ዕቅድ መሰረት ሎት 1 የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፤ ሎት 2 የመኪና ጎማዎች እና ሎት 3 ለስፖርት ምከር ቤት የስፖርት ትጥቅ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስስዚህ፡-

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ያላቸውና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. የግዥ መጠናቸው 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይበሆኑ ግዥዎች የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፤

3. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈልና ገንዘብ ያዥ ላይ ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ጎዛምን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ፡፡

4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለእያንዳንዱ ተጫራቾች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) በማስላት በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክበተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለዋና ገንዘብ ያዥ በመሂ-ı ገቢ አድርገው ከጨረታ ሰነዱ ጋርሲፒኦ ብለው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. የጨረታ መክፈቻ ቀኑን በተመለከተ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ ሲሸጥ ይቆይና በ16ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ተዘጋጅቶ የተሠጣቸውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የይዘት ለውጥ ወይም ማሻሻያ ሳያደርጉ ሞልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሆኖም _ የተሠጠው ሰነድ ላይ የግልፅነት ማብራሪያ ካስፈለገ ደውለው ወይም በአካል ቀርበው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ፊርማቸውን በማድረግ፣ ማህተም በመርገጥና በፖስታ በማሸግና ፖስታው ላይ አድራሻ በመፃፍ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

8. ተጫራቾች የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር መገለጫ /ተፈላጊነት ደረጃ/ በግዥ ቡድናችን ከተዘጋጀው መደበኛ የጨረታ ሠነድ ላይ ማየት ይችላሉ፡፡ ለሚገዙ ግዥዎች ናሙና የግዥ ቡድናችን ቢሮ ላይ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡

9. ግዥ ፈፃሚ መ/ቤት የጨረታ ውድድርን በሎት ዋጋ (በጥቅል ዋጋ ድምር) የሚያወዳድር ሲሆን ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች አሸናፊ ሆኖ የሚመረጥ ይሆናል፡፡

10. የዕቃ አቅርቦት ጥራት ችግር አንዳይከሠት በሚመለከታቸው ባለሙያዎች እየተረጋገጡ የዕቃዎች ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡

11. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

13. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር-8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም

በስልክ ቁጥር 058-1-78-01-30/058-7-71-14-22 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎዛምን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስ/ቡድን

Save Tender