አዋሽ ባንክ የባንኩን ተሽከርካሪዎች ሰርቪስ ለማስደረግና ለማስጠገን ብቁ የሆኑ ጋራዦችን በጨረታ አወዳድሮ ለ12 ወራት (ለአንድ አመት) በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Awash Bank S.C (አዋሽ ባንክ አ.ማ)
የተሽከርካሪ ጥገና ጨረታ ማስታወቂያ (Invitation to bid)
የጨረታ ቁጥር-AB-07/2025-26.
- አዋሽ ባንክ የባንኩን ተሽከርካሪዎች ሰርቪስ ለማስደረግና ለማስጠገን ብቁ የሆኑ ጋራዦችን በጨረታ አወዳድሮ ለ12 ወራት (ለአንድ አመት) በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው በተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚገልፅ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እና የመንግስት ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒአ ወይም ቅድመ ሁኔታን ባላስቀመጠ (Unconditional and Irrevocable) ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት ከሰኞ ዓርብ ከ 2፡00-6፡00 ሰዓት እና ከ 7፡00-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ 2፡00-6፡00 ሰዓት በቅድሚያ በማንኛውም አዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 01540000544500 የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ገቢ በማድረግና ገቢ ማድረጋቸውን የሚያረጋግጥ ደረሰኝ በማቅረብ የባንኩ ዋና መ/ ቤት ህንፃ 12ኛ ፎቅ በሚገኘው የባንኩ ግዥ ዋና ክፍል ቢሮ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን ሠነዶች በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተራ ቁጥር 4 በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በእለቱ ነሐሴ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ከላይ በተራ ቁጥር 4 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ዋጋ የሚፀናበት ጊዜ (bid validity period) ከቴክኒካል ከፈታው ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ 120 ቀናት ነው።
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 ያሉትን መስፈርት ያላሟሉ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-57-11-07 ወይም 0115-57-00-84 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አዋሽ ባንክ አክሲዮን ማህበር
