Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕ/ኢት/ክ/መ/በሀድያ ዞን የአመካ ወ/ፋ/ጽ/ቤት
  • Address ሀድያ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-93-42-04-60
  • Website
  • Deadline08 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Security10,000 / አሥር ሺህ ብር/
  • opening date2025-09-08 00:00:00
  • Categories Stationery Materials

በሀዲያ ዞን የአመካ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳችን መ/ቤቶች የጽሕፈት መሣሪያ ለመግዛት ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በማዕ/ኢት/ክ/መ/በሀድያ ዞን የአመካ ወ/ፋ/ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሀዲያ ዞን የአመካ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳችን መ/ቤቶች የጽሕፈት መሣሪያ ለመግዛት ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ
  2. ካት እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ሆኖ የጨረታውን ሰነድ ከአመካ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ፡፡
  3. ጨረታው አየር ላይ የሚቆየው ለ15 ተከታታይ ቀናት ሆኖ በ15ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በ5፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈት ሂደቱን አያስተጓጉልም፡፡
  4. የጨረታ መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በጨረታው በተገለጸው መሠረት በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 / አሥር ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይንም ካሽ ከጨረታ ሰነድ ጋር ይዞ መቅረብ የሚችል፤
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ታክስን የሚያካትት መሆኑን መግለጽ አለባቸው ታክስ በትክክል ካልተገለጸ የቀረበው ዋጋ ታክስን እንዳካተተ ተደርጎ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡
  7. የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን በፖስታ አሽገው የድርጅቱን ስም፣ ማህተምና ስልክ ቁጥር መጻፍ አለባቸው፡፡
  8. ከጨረታ መዝጊያ ጊዜ በኋላ ዘግይቶ የመጣ ኤንቨሎፕ ተቀባይነት አይኖረውም፤ እንደታሸገ ለተጫራቹ ይመለሳል፡፡
  9. በጨረታ ለተሸነፉት ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ወይንም ብር አሸናፊ ከተለየ በኋላ ይሰጣቸዋል፡፡
  10. አሸናፊ የሚለየው በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
  11. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ወጪ እስከ አመካ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት አድርሶ ማስረከብ የሚችል፡፡
  12. ባቀረበው ዕቃዎች ላይ የጥራት ችግር ካጋጠመ በራሱ ኪሳራ መቀየር የሚችል፤ ካልቀየረ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
  14. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-93-42-04-60 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡

 

በማዕ/ኢት/ክ/መ/በሀድያ ዞን የአመካ ወ/ፋ/ጽ/ቤት

 

Save Tender