የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለከተማ ውስጥ ለአረንጓዴ ልማት የውሃ ቦቲ መኪና ኪራይ ውሃ ለማጠጣት የሻወር ውስጥ ትራክ ቦቲ /shower truk/ አገልግሎት ግዥን በኪራይ ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጀት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ለከተማ ውስጥ ለአረንጓዴ ልማት የውሃ ቦቲ መኪና ኪራይ ውሃ ለማጠጣት የሻወር ውስጥ ትራክ ቦቲ /shower truk/ አገልግሎት ግዥን በኪራይ ለመፈጸም እንዲቻል በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ድርጀት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚገዙ ዕቃዎች፤
- ሎት/ ምድብ-1
- ሎት /ምድብ-2
- ሎት/ ምድብ-3
- ሎት/ ምድብ-4
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡-
- በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 300/ ሶስት መቶ ብር/ በባንክ አካውንት በመክፈል ሰነዱ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ ፋይናሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ እና ቴክኒካል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በመያዝ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ ከ3፡00-4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ጨረታው ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን በዓል ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታ አከፋፈት ሥነ-ሥርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱ መካከል ከ2% በላይም ሆነ በታች ልዩነት ካለ ተጫራቹ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበው መሀንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ላይ ከ15% በላይከሆነ ቀጥታ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ያስገቡት ዋጋ ከቀረበው መሀንዲስ ዋጋ ጥናት ጋር ሲነፃፀር ወደ ታች ከ15% በታች ከሆነ ለእያንዳንዱ ስራ ዝርዝር ተጨባጭ የወቅቱ ገበያ ዋጋ ትንተና (Direct unit cost analysis sheet) ማቅረብ የሚችል እና ለዚህም መ/ቤቱ የጠየቀውን ውል ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ወይም መያዣ ገንዘብ መጠን ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-220-99-63/046-21213-34
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
ሀዋሳ
